‘ትናንትና የናቡቴንና የልጆቹን መገደል አየሁ፤ በዚሁ እርሻ ላይ እንደምቀጣህ እምላለሁ’ የሚል ነበር።” ስለዚህ ኢዩ “እግዚአብሔር የተናገረው ቃል ይፈጸም ዘንድ የኢዮራምን ሬሳ አንሥተህ የናቡቴ ርስት በነበረው እርሻ ላይ በመወርወር ጣለው” ሲል የቅርብ ረዳቱን አዘዘ።
2 ዜና መዋዕል 6:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ሆይ፥ በሰማይ ሆነህ ስማ፤ ለአገልጋዮችህም ፍርድን ስጥ፤ ይኸውም በደል የሠራውን ሰው በጥፋቱ መጠን እንዲቀጣ፥ ንጹሑም ነጻ እንዲወጣ አድርግ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከሰማይ ሆነህ ስማ፤ አድርግም። በደለኛውን፣ በደሉን በራሱ ላይ አድርገህ እንደ ሥራው በመክፈል በባሪያዎችህ መካከል ፍረድ። ንጹሑም በደለኛ አለመሆኑን አስታውቅ፤ እንደ ንጽሕናውም ክፈለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንተ በሰማይ ሆነህ ስማ፥ አድርግም፥ በባርያዎችህንም ፍረድ፥ በደለኛውንም እንደ በደሉ ክፈለው፥ መንገዱንም በራሱ ላይ መልስበት፤ ንጹሑንም አጽድቀው፥ እንደ ጽድቁም ክፈለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሰማይ ስማ፤ አድርግም፤ በባሪያዎችህም ላይ ዳኛ ሁን፤ በበደለኛውም ላይ ፍረድ፤ መንገዱንም በራሱ ላይ መልስበት፤ ንጹሑንም አጽድቀው፤ እንደ ጽድቁም ክፈለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሰማይ ስማ፤ አድርግም፤ በባሪያዎችህም ላይ ዳኛ ሁን፤ በበደለኛውም ላይ ፍረድ፤ መንገዱንም በራሱ ላይ መልስበት፤ ንጹሑንም አጽድቀው፤ እንደ ጽድቁም ክፈለው። |
‘ትናንትና የናቡቴንና የልጆቹን መገደል አየሁ፤ በዚሁ እርሻ ላይ እንደምቀጣህ እምላለሁ’ የሚል ነበር።” ስለዚህ ኢዩ “እግዚአብሔር የተናገረው ቃል ይፈጸም ዘንድ የኢዮራምን ሬሳ አንሥተህ የናቡቴ ርስት በነበረው እርሻ ላይ በመወርወር ጣለው” ሲል የቅርብ ረዳቱን አዘዘ።
“አንድ ሰው ባልንጀራውን መበደሉን የሚገልጥ ክስ ቀርቦበት በዚህ ቤተ መቅደስ ውስጥ ወደሚገኘው መሠዊያ አምጥተውት ከበደል ንጹሕ መሆኑን በመሐላ በሚያረጋግጥበት ጊዜ፥
አምላክ ሆይ! አንተ ግን ችግርንና ጭንቀትን አይተህ ልታስወግዳቸው መፍትሔ ታዘጋጃለህ፤ ችግረኛ ራሱን ለአንተ ይሰጣል፤ አንተም የሙት ልጆችን ትረዳለህ።
አጥፊዎች በባቢሎን ላይ ስለ ዘመቱ ወታደሮችዋ ተማረኩ፤ ቀስታቸውም ተሰባበረ፤ እኔ ለሁሉም እንደየሥራው ዋጋውን የምከፍል አምላክ ስለ ሆንኩ፥ ባቢሎን በፈጸመችው ግፍ መጠን ፍዳዋን እከፍላታለሁ።
ሞት የሚገባው ኃጢአት ለሚሠራ ሰው ብቻ ነው፤ ልጅ ስለ አባቱ ኃጢአት አይቀጣም፤ አባትም ስለ ልጁ ኃጢአት አይቀጣም፤ ደግ ሰው በደግነቱ መልካም ዋጋውን ያገኛል፤ ክፉ ሰውም በክፋቱ ይቀጣል።
ሴትዮዋ ራስዋን እያረከሰች በባልዋ ላይ ያመነዘረች ከሆነች፥ ውሃው ብርቱ ሥቃይን ያስከትልባታል፤ ይኸውም ሆድዋ ያብጣል፤ ማሕፀንዋም ይኰማተራል፤ ስምዋም በሕዝብዋ መካከል የተረገመ ሆኖ ይቀራል፤