2 ዜና መዋዕል 27:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በኢዮአታም ዘመነ መንግሥት የተፈጸመው ሌላው ድርጊት ሁሉ፥ ያካሄደው ጦርነትና የመንግሥቱ አመራር ሁሉ በእስራኤልና በይሁዳ ነገሥታት የታሪክ መጻሕፍት ተመዝግበው ይገኛሉ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በኢዮአታም ዘመነ መንግሥት የተከናወነው ሌላው ተግባር፣ ያደረጋቸው ጦርነቶችና አካሄዱ ሁሉ በእስራኤልና በይሁዳ ነገሥታት መጽሐፍ ተጽፏል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የቀረውም የኢዮአታም ነገር፥ ያደረገውም ጦርነት ሁሉ፥ ሥራውም፥ እነሆ፥ በእስራኤልና በይሁዳ ነገሥታት መጽሐፍ ተጽፎአል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የቀሩትም የኢዮአታም ነገሮች፥ ሰልፉም ሁሉ፥ ሥራውም፥ እነሆ፥ በእስራኤልና በይሁዳ ነገሥታት መጽሐፍ ተጽፎአል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የቀረውም የኢዮአታም ነገር፥ ሰልፉም ሁሉ፥ ሥራውም፥ እነሆ፥ በእስራኤልና በይሁዳ ነገሥታት መጽሐፍ ተጽፎአል። |
ኢዮሣፍጥ ከነገሠበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ዘመነ መንግሥቱ ፍጻሜ ድረስ ያደረገው ሌላው ነገር ሁሉ ከእስራኤል ነገሥታት ታሪክ ክፍል አንዱ በሆነው በሐናኒ ልጅ በኢዩ ታሪክ ውስጥ ተመዝግቦ ይገኛል።
አሜስያስ በዘመነ መንግሥቱ ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ ያደረገው ሌላው ነገር ሁሉ በይሁዳና በእስራኤል ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ተመዝግቦ ይገኛል።