ኢዮራም በሠላሳ ሁለት ዓመቱ ነገሠ፤ መኖሪያውንም በኢየሩሳሌም አድርጎ ስምንት ዓመት ገዛ፤ እርሱ በሞተ ጊዜ ማንም አላዘነለትም፤ በዳዊት ከተማ ቀበሩት፤ ይሁን እንጂ በነገሥታት መካነ መቃብር አልተቀበረም።
2 ዜና መዋዕል 26:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዖዝያ ሞተ፤ በነገሥታትም መካነ መቃብር አጠገብ ባለው ስፍራ ቀበሩት፤ በነገሥታት መካነ መቃብር ያልተቀበረው የቆዳ በሽታ ስለ ነበረበት ነው፤ በእርሱም እግር ተተክቶ ልጁ ኢዮአታም ነገሠ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዖዝያንም ከአባቶቹ ጋራ አንቀላፋ። ሕዝቡም “ለምጽ አለበት” ብለው የነገሥታቱ በሆነው መቃብር አጠገብ ባለው ቦታ ቀበሩት፤ ልጁም ኢዮአታም በምትኩ ነገሠ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዖዝያንም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፥ እነርሱም፦ “ለምጻም ነው” ብለው ከአባቶቹ ጋር በነገሥታቱ መቃብር እርሻ ውስጥ ቀበሩት፤ ልጁም ኢዮአታም በእርሱ ፋንታ ነገሠ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዖዝያንም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ ለምጻም ነው ብለዋልና የነገሥታቱ መቃብር ባልሆነ እርሻ ውስጥ ቀበሩት፤ ልጁም ኢዮአታም በእርሱ ፋንታ ነገሠ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዖዝያንም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ ለምጻም ነው ብለውም ከአባቶቹ ጋር በነገሥታቱ መቃብር እርሻ ውስጥ ቀበሩት፤ ልጁም ኢዮአታም በእርሱ ፋንታ ነገሠ። |
ኢዮራም በሠላሳ ሁለት ዓመቱ ነገሠ፤ መኖሪያውንም በኢየሩሳሌም አድርጎ ስምንት ዓመት ገዛ፤ እርሱ በሞተ ጊዜ ማንም አላዘነለትም፤ በዳዊት ከተማ ቀበሩት፤ ይሁን እንጂ በነገሥታት መካነ መቃብር አልተቀበረም።
እንዲህም አሉት፦ “ዖዝያ ሆይ! አንተ ለእግዚአብሔር ዕጣን ታጥን ዘንድ አይገባህም፤ ይህን ለማድረግ የተመደቡት ለእግዚአብሔር የተለዩት የአሮን ልጆች የሆኑት ካህናት ብቻ ናቸው፤ ስለዚህ ከዚህ ከተቀደሰው ስፍራ ውጣ፥ እግዚአብሔር አምላክን አሳዝነሃል፤ ይህም ከእግዚአብሔር ዘንድ ክብርን የሚያስገኝልህ ድርጊት አይደለም።”
ኢዮአታም ዕድሜው ኻያ አምስት ዓመት ሲሆነው ነገሠ፤ መኖሪያውንም በኢየሩሳሌም አድርጎ ዐሥራ ስድስት ዓመት ገዛ፤ እናቱም ይሩሻ ተብላ የምትጠራ የሳዶቅ ልጅ ነበረች።
ንጉሥ አካዝ ሞተ፤ በኢየሩሳሌምም ተቀበረ፤ ይሁን እንጂ በነገሥታት መካነ መቃብር አልተቀበረም፤ በእርሱም እግር ተተክቶ ልጁ ሕዝቅያስ ነገሠ።
ንጉሡ ዖዝያን በሞተበት ዓመት እግዚአብሔርን አየሁት፤ እርሱም ከፍ ባለና ልዕልና ባለው ዙፋን ላይ ተቀምጦ መጐናጸፊያውም ቤተ መቅደሱን ሞልቶት ነበር።