ፊታችንን ወደዚህ ቤተ መቅደስ መልሰን በምንጸልይበት ጊዜ የእኔንና የሕዝብህን ጸሎት ስማ፤ ከመኖሪያህ ከሰማይ ሆነህ ስማን፤ ይቅርም በለን።
2 ዜና መዋዕል 20:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ‘እኛን ለመቅጣት ጦርነትን፥ ቸነፈርን ወይም ራብን የመሳሰለውን መቅሠፍት ብታደርስብን የአንተ ስም ወደሚጠራበት ወደዚህ ቤተ መቅደስ ፊት ለፊት መጥተን በመቆም ከመከራችን እንድታድነን ወደ አንተ እንጸልያለን፤ አንተም ጸሎታችንን ሰምተህ በመታደግ ታድነናለህ’ ብሎ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ‘የፍርድ ሰይፍም ሆነ የቸነፈር ወይም የራብ መከራ ቢደርስብን፣ ስምህ በተጠራበት በዚህ ቤተ መቅደስ ፊት ለፊት፣ በፊትህ ቆመን በጭንቀታችን ወደ አንተ እንጮሃለን፤ አንተም ትሰማናለህ፤ ታድነናለህም።’ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ‘ክፉ ነገር፥ ሰይፍ ወይም ፍርድ ወይም ቸነፈር ወይም ራብ፥ ቢመጣብን ስምህ ባለበት በዚህ ቤት ፊትና በፊትህ ቆመን በመከራችን ወደ አንተ እንጮሃለን፥ አንተም ሰምተህ ታድነናለህ።’ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዲህም አሉ፦ ክፉ ነገር፥ የፍርድ ሰይፍ ወይም ቸነፈር ወይም ራብ፥ ቢመጣብን በዚህ ቤት ፊትና በፊትህ እንቆማለን፤ ስምህ በዚህ ቤት ላይ ነውና፤ በመከራችንም ወደ አንተ እንጮኻለን፥ አንተም ሰምተህ ታድነናለህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ‘ክፉ ነገር፥ የፍርድ ሰይፍ ወይም ቸነፈር ወይም ራብ፥ ቢመጣብን ስምህ ባለበት በዚህ ቤት ፊትና በፊትህ ቆመን በመከራችን ወደ አንተ እንጮሃለን፤ አንተም ሰምተህ ታድነናለህ’ አሉ። |
ፊታችንን ወደዚህ ቤተ መቅደስ መልሰን በምንጸልይበት ጊዜ የእኔንና የሕዝብህን ጸሎት ስማ፤ ከመኖሪያህ ከሰማይ ሆነህ ስማን፤ ይቅርም በለን።
“ሕዝብህ እስራኤል በደል ሠርተው አንተን በማሳዘናቸው ምክንያት በጠላቶቻቸው ድል ሲሆኑ ተጸጽተውም ወደ አንተ በመመለስ ወደዚህ ቤተ መቅደስ ቢመጡና የአንተን ይቅርታ ለማግኘት ራሳቸውን ዝቅ አድርገው በትሕትና ቢለምኑህ፥
“በምድሪቱ ላይ ረሀብ ወይም ቸነፈር በሚመጣበት ጊዜ፥ እንዲሁም በውርጭ በዋግና በአንበጣ ወይ በኩብኩባ መንጋ በሚወድምበት ጊዜ፥ ወይም ጠላቶቻቸው በሕዝብ ላይ አደጋ በሚጥሉበት ጊዜ፥ ወይም በሕዝብህ ላይ ልዩ በሽታና ደዌ በሚደርስባቸው ጊዜ፥
‘ሕዝቤን ከግብጽ ካወጣሁበት ጊዜ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ በስሜ ቤተ መቅደስ የሚሠራበት ስፍራ ከመላው የእስራኤል ምድር አንድም ከተማ፥ እንዲሁም ሕዝቤን እስራኤልን የሚመራ ማንንም ሰው አልመረጥኩም ነበር፤
ዕዝራ በቤተ መቅደሱ ፊት ለፊት ለጸሎት ተንበርክኮ እያለቀሰ የተፈጸመውን ኃጢአት ሁሉ ለእግዚአብሔር በሚናዘዝበት ጊዜ ወንዶችም፥ ሴቶችም፥ ሕፃናትም ጭምር ያሉበት ቊጥሩ የበዛ የእስራኤል ማኅበር መጥቶ በዙሪያው በመሰብሰብ በመረረ ሁኔታ ያለቅሱ ነበር።
ለእኔ ከጭቃ የተሠራ መሠዊያ አብጁልኝ፤ በእርሱም ላይ ከበጎቻችሁ፥ ከፍየሎቻችሁና ከከብቶቻችሁ መርጣችሁ የሚቃጠልና የአንድነት መሥዋዕት አድርጋችሁ ሠዉበት፤ ስሜ እንዲታሰብበት በወሰንኩት ስፍራ ሁሉ ወደ እናንተ መጥቼ እባርካችኋለሁ፤
የሚነግርህን በማዳመጥ ለእርሱ ታዘዝ፤ በእርሱም ላይ አታምፅ፤ ለእርሱ ሙሉ ሥልጣን የሰጠሁት ስለ ሆነ የምትፈጽመውን ዐመፅ እየተመለከተ ይቅርታ አያደርግልህም።