2 ዜና መዋዕል 19:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሚከተለውንም መመሪያ ሰጣቸው፤ “እግዚአብሔርን በመፍራት በታማኝነትና በቅን ልቡና አገልግሉ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነርሱንም እንዲህ ብሎ አዘዛቸው፤ “እግዚአብሔርን በመፍራት፣ በታማኝነትና በፍጹም ልብ አገልግሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲህም ብሎ አዘዛቸው፦ “እንዲህ ስታደርጉ ጌታን በመፍራት በቅንነትም በፍጹምም ልብ አድርጉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዲህም ብሎ አዘዛቸው፥ “እንዲሁ እግዚአብሔርን በመፍራት፥ በቅንነትም፥ በፍጹምም ልብ አድርጉ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲህም ብሎ አዘዛቸው “እንዲሁ እግዚአብሔርን በመፍራት በቅንነትም በፍጹምም ልብ አድርጉ። |
እግዚአብሔር መላውን ዓለም አተኲሮ በመመልከት፥ በሙሉ ልባቸው በእርሱ ለሚተማመኑት ሁሉ ብርታትን ይሰጣቸዋል፤ እንግዲህ አንተ የሞኝነት ሥራ ስለ ፈጸምክ ከእንግዲህ ወዲህ ጦርነት አይለይህም፤”
በከተሞች ከተቀመጡት ከወገኖቻችሁ ወደ እናንተ የሚመጣ ጉዳይ፥ የግድያ፥ ወይም ሌላ የሕግ ጉዳይ፥ ሕግን፥ ትእዛዞችን ወይም ድንጋጌና ሥርዓቶችን መተላለፍ ቢሆን በእግዚአብሔር ላይ በደል እንዳይፈጽሙ፥ ቊጣም በእናንተና በወንድሞቻችሁ ላይ እንዳይመጣ አስጠንቅቁአቸው፤ እንዲህም ብታደርጉ በደለኞች አትሆኑም።
ፍትሕ ማጓደል ወይም ማድላት ወይም ጉቦ መቀበል በአምላካችን በእግዚአብሔር ዘንድ የሌሉ ስለ ሆነ እግዚአብሔርን በመፍራት ትክክለኛ ፍርድ ስጡ።”
ንጉሥ ኢዮሣፍጥ የእግዚአብሔርን ሕግ በመተላለፍ ወይም በከተማይቱ ኗሪዎች መካከል የሚነሣውን ሕግ ነክ ክርክር በሚመለከት ጉዳይ ሁሉ ይዳኙ ዘንድ ሌዋውያንን፥ ካህናትንና ከታወቁ የአገር ሽማግሌዎች አንዳንዶቹን በኢየሩሳሌም ሾመ፤ እነርሱም በኢየሩሳሌም ተቀመጡ።