2 ዜና መዋዕል 19:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲህ የሚል መመሪያም ሰጣቸው፦ “ፍርድ በምትሰጡበት ጊዜ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር መሆኑን በመገንዘብ ብርቱ ጥንቃቄ አድርጉ፤ እናንተ የምትፈርዱት ሰውን ለማስደሰት ሳይሆን ለእግዚአብሔር ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲህም አላቸው፤ “እናንተ የምትፈርዱት ለሰው ሳይሆን፣ ፍርድ በምትሰጡበት ጊዜ ሁሉ ከእናንተ ጋራ ለሆነው ለእግዚአብሔር ስለ ሆነ፣ በምትሰጡት ውሳኔ ሁሉ ብርቱ ጥንቃቄ አድርጉ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፈራጆቹንም እንዲህ አላቸው፦ “ለጌታ እንጂ ለሰው አትፈርዱምና፥ እርሱም በፍርድ ነገር ከእናንተ ጋር ነውና የምታደርጉትን ልብ ብላችሁ ተገንዘቡ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፈራጆቹንም፥ “ለእግዚአብሔር እንጂ ለሰው አትፈርዱምና፥ የፍርድም ነገር ከእናንተ ጋር ነውና የምታደርጉትን ተመልከቱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፈራጆቹንም “ለእግዚአብሔር እንጂ ለሰው አትፈርዱምና፥ እርሱም በፍርድ ነገር ከእናንተ ጋር ነውና የምታደርጉትን ተመልከቱ። |
በአንድ አገር ግፍ ሲሠራና መብት በመንፈግ ፍትሕ ሲጓደል ባየህ ጊዜ አትደነቅ፤ እያንዳንዱ ገዥ የበላይ ተመልካች አለው፤ ከሁሉም በላይ የሆነ ሌላ ተመልካች ደግሞ አለ።
“የፍርድ ውሳኔ በምትሰጡበት ጊዜ ታማኞችና ትክክለኞች ሁኑ፤ ለሁሉም በትክክል ፍረዱ እንጂ ለድኻው ስለ ድኽነቱ አድልዎ አታድርጉለት፤ ባለጸጋውንም ስለ ሀብቱ ብዛት አትፍሩት።
ኢየሱስ እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “እንዳትሳሳቱ ተጠንቀቁ! ብዙዎች ‘እኔ ክርስቶስ ነኝ! እነሆ፥ ጊዜው ቀርቦአል!’ እያሉ በስሜ ይመጣሉ፤ እነርሱን አትከተሉአቸው።
በምትሰጡትም ውሳኔ አድልዎ አታድርጉ፤ ስለ ማንኛውም ታላቅም ሆነ ታናሽ ሰው ያለ አድልዎ በእኩልነት ፍረዱ። ፍርድ የእግዚአብሔር ስለ ሆነ ማንንም አትፍሩ፤ ለእናንተ የሚከብድባችሁ ነገር ቢኖር ወደ እኔ አምጡት፤ እኔም ውሳኔ እሰጥበታለሁ፤’
ሙሴ የሰጣችሁን ሕግና ትእዛዞች በጥንቃቄ ፈጽሙ፤ ይኸውም አምላካችሁን እግዚአብሔርን ውደዱ፤ ፈቃዱን ፈጽሙ፤ ትእዛዙንም ጠብቁ፤ ለእርሱም ታማኞች ሆናችሁ በሙሉ ልባችሁ፥ በፍጹም ሐሳባችሁ አገልግሉት።”