2 ዜና መዋዕል 18:30 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሶርያ ንጉሥም “የእስራኤል ንጉሥ አክዓብን ነጥላችሁ ግደሉ እንጂ በሌላ በማንም ላይ አደጋ አትጣሉ” ሲል ለሠረገላ ጦር አዛዦች ትእዛዝ አስተላለፈ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚህ ጊዜ የሶርያ ንጉሥ የሠረገላ አዛዦቹን፣ “ከእስራኤል ንጉሥ በቀር፣ ትንሽም ሆነ ትልቅ ከሌላ ከማንም ጋራ እንዳትዋጉ” ብሎ አዝዟቸው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሶርያም ንጉሥ የሰረገሎቹን አለቆች እንዲህ ብሎ አዝዞ ነበር፦ “ከእስራኤል ንጉሥ በቀር ትንሽ ቢሆን ወይም ትልቅ ከማናቸውም ጋር አትዋጉ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሶርያም ንጉሥ ከእርሱ ጋር የነበሩትን የሰረገሎቹን አለቆች፦ ከእስራኤልም ንጉሥ በቀር ትንሽ ቢሆን ወይም ትልቅ ከማናቸውም ጋር አትጋጠሙ ብሎ አዝዞ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሶርያም ንጉሥ የሰረገሎቹን አለቆች “ከእስራኤል ንጉሥ በቀር ትንሽ ቢሆን ወይም ትልቅ ከማናቸውም ጋር አትጋጠሙ” ብሎ አዝዞ ነበር። |
ከዚህ በኋላ ያ ነቢይ ንጉሡን እንዲህ አለው፤ “እግዚአብሔር የተናገረው ቃል ይህ ነው፤ ‘እኔ ይገደል’ ብዬ የፈረድኩበትን ሰው እንዲያመልጥ ስለ ፈቀድህ በእርሱ ፈንታ አንተ በሞት ትቀጣለህ፤ የዚያ ሰው ሠራዊት አምልጦ እንዲሄድ ስላደረገ ሠራዊትህም ይደመሰሳል፤ ”
የእስራኤልን አምላክ እግዚአብሔርን የማያመልክ ማንም ወጣት ወይም ሽማግሌ፥ ወንድ ወይም ሴት ቢሆን በሞት የሚቀጣ መሆኑን በመሐላ ቃል አረጋገጡ፤
አክዓብም ኢዮሣፍጥን “ወደ ጦርነት ለመሄድ ስንነሣ እኔ ሌላ ሰው መስዬ ለመታየት ሌላ ልብስ እለብሳለሁ፤ አንተ ግን ልብሰ መንግሥትህን ልበስ” አለው፤ ስለዚህ የእስራኤል ንጉሥ አክዓብ ሌላ ልብስ ለብሶ ማንነቱን በመሰወር ዘመተ።
ስለዚህ ንጉሥ ኢዮሣፍጥን ባዩ ጊዜ የእስራኤል ንጉሥ ስለ መሰላቸው በእርሱ ላይ አደጋ ለመጣል ከበቡት፤ ነገር ግን ኢዮሣፍጥ ጮኸ፤ እግዚአብሔር አምላክም ከእነርሱ እጅ በመታደግ አዳነው፤ እነርሱም በእርሱ ላይ አደጋ ከመጣል ተገቱ።
በምትሰጡትም ውሳኔ አድልዎ አታድርጉ፤ ስለ ማንኛውም ታላቅም ሆነ ታናሽ ሰው ያለ አድልዎ በእኩልነት ፍረዱ። ፍርድ የእግዚአብሔር ስለ ሆነ ማንንም አትፍሩ፤ ለእናንተ የሚከብድባችሁ ነገር ቢኖር ወደ እኔ አምጡት፤ እኔም ውሳኔ እሰጥበታለሁ፤’