ከእነርሱም አንዱ የከናዕና ልጅ ሴዴቅያስ ከብረት ቀንዶችን ሠርቶ አክዓብን “እግዚአብሔር ‘በእነዚህ ቀንዶች ሶርያውያንን ወግተህ ፍጹም የሆነ ድልን ትቀዳጃለህ’ ይልሃል” አለው።
2 ዜና መዋዕል 18:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የከናዕና ልጅ ሴዴቅያስ ወደ ሚክያስ ቀረብ ብሎ በጥፊ መታውና “ኧረ ከመቼ ወዲህ ነው የእግዚአብሔር መንፈስ ከእኔ አልፎ አንተን ያነጋገረህ?” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም የክንዓና ልጅ ሴዴቅያስ ወጥቶ ሚክያስን በጥፊ መታውና፣ “ለመሆኑ የእግዚአብሔር መንፈስ በየት በኩል ዐልፎኝ ነው አንተን ያናገረህ?” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የክንዓናም ልጅ ሴዴቅያስ ቀረበ፥ ሚክያስንም በጥፊ መታውና እንዲህ አለ፦ “የጌታ መንፈስ ከአንተ ጋር ለመነጋገር በምን ዓይነት መንገድ ከእኔ አለፈ?” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የካህናንም ልጅ ሴዴቅያስ ቀረበ፤ ሚክያስንም በጥፊ መታውና፥ “የእግዚአብሔር መንፈስ ከአንተ ጋር ይናገር ዘንድ በምን መንገድ ከእኔ አለፈ?” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የክንዓናም ልጅ ሴዴቅያስ ቀረበ፤ ሚክያስንም በጥፊ መታውና “የእግዚአብሔር መንፈስ ከአንተ ጋር ይናገር ዘንድ በምን መንገድ ከእኔ አለፈ?” አለ። |
ከእነርሱም አንዱ የከናዕና ልጅ ሴዴቅያስ ከብረት ቀንዶችን ሠርቶ አክዓብን “እግዚአብሔር ‘በእነዚህ ቀንዶች ሶርያውያንን ወግተህ ፍጹም የሆነ ድልን ትቀዳጃለህ’ ይልሃል” አለው።
አንዳንዶችም ምራቃቸውን እንትፍ ይሉበት ጀመር፤ ዐይኑንም በጨርቅ ሸፍነው “አንተ ነቢይ ከሆንክ እስቲ ማን እንደ መታህ ዕወቅ!” እያሉ በቡጢ ይመቱት ነበር። ሎሌዎችም በጥፊ እየመቱ ወሰዱት።