2 ዜና መዋዕል 17:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢዮሣፍጥ በአባቱ በአሳ እግር ተተክቶ ነገሠ፤ እስራኤልንም ለመውጋት ኀይሉን አጠናከረ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ልጁ ኢዮሣፍጥ በርሱ ፈንታ ነገሠ፤ በእስራኤል ላይ በረታ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በእርሱ ፋንታ ልጁ ኢዮሣፍጥ በየይሁዳ ላይ ነገሠ፥ በእስራኤልም ላይ ኃይሉን አጠናከረ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከአሳም በኋላ ልጁ ኢዮሳፍጥ ነገሠ፤ ኢዮሳፍጥም በእስራኤል ላይ ጠነከረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በእርሱ ፋንታ ልጁ ኢዮሳፍጥ ነገሠ፤ በእስራኤልም ላይ ጠነከረ። |
እግዚአብሔር በኤልያስ አማካይነት በተናገረውም ቃል መሠረት አካዝያስ ሞተ፤ አካዝያስ ወንዶች ልጆች ስላልነበሩት በእርሱ እግር ተተክቶ ወንድሙ ኢዮራም ነገሠ፤ ይህም የሆነው የኢዮሣፍጥ ልጅ ኢዮራም በይሁዳ በነገሠ በሁለተኛው ዓመት ነበር።
ዝነኞች የሆኑት የዳዊት ወታደሮች ስም ዝርዝር ከዚህ በታች እንደሚከተለው ነው፦ እነርሱም ከሌሎቹ እስራኤላውያን ጋር ሆነው እግዚአብሔር በሰጠው የተስፋ ቃል መሠረት ዳዊት እንዲነግሥ በጣም ረድተዋል። መንግሥቱም ጽኑና ኀያል እንዲሆን አድርገዋል።
በተመሸጉት የይሁዳ ከተሞችና በየገጠሩ ሁሉ እንዲሁም አባቱ ንጉሥ አሳ ድል አድርጎ በያዛቸው በኤፍሬም ግዛት ባሉት ከተሞች ሁሉ ወታደሮቹን አሰፈረ፤
ንጉሥ ሕዝቅያስም ቅጽሮችን ጠግኖ በላያቸው ላይ የመቈጣጣሪያ ግንቦችን በመሥራትና ከውጪም በኩል ቅጽሮችን በመገንባት የከተማይቱን መከላከያዎች አጠናከረ፤ በተጨማሪም ከጥንታዊት ኢየሩሳሌም በስተ ምሥራቅ በኩል በሚገኘው በተደለደለው ቦታ ላይ የተሠሩትን መከላከያዎች አደሰ፤ ብዙ ጦርና ጋሻም ሠራ።
ንጉሡ ያለቅሳል፤ መስፍኑም ሙሉ በሙሉ ተስፋ ይቈርጣል፤ ሕዝቡም ከፍርሃት የተነሣ ይርበደበዳሉ፤ እንደ አካሄዳችሁ እቀጣችኋለሁ፤ በሌሎች ላይ በፈረዳችሁት ዐይነት እፈርድባችኋለሁ፤ በዚህም እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ታውቃላችሁ።”
የሳኦል ልጅ ዮናታንም እዚያው ድረስ ወደ ዳዊት ሄዶ እግዚአብሔር በአስተማማኝ ሁኔታ የሚጠብቀው መሆኑን በመግለጥ እንዲህ እያለ አበረታታው፤