2 ዜና መዋዕል 14:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሥ አሳ ታላላቅ ጋሻና ጦር የታጠቁ ሦስት መቶ ሺህ ሠራዊት ከይሁዳ፥ ታናናሽ ጋሻና ቀስት የያዙ ሁለት መቶ ሰማኒያ ሺህ ሠራዊት ከብንያም ነበሩት፤ እነዚህ ሁሉ በሚገባ የሠለጠኑ ጀግኖች ወታደሮች ነበሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አሳ ታላላቅ ጋሻና ጦር የያዙ ሦስት መቶ ሺሕ የይሁዳ ሰዎች እንዲሁም ጋሻና ቀስት የያዙ ሁለት መቶ ሰማንያ ሺሕ የብንያም ሰዎች ነበሩት፤ እነዚህ ሁሉ ብርቱ ተዋጊዎች ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለአሳም አላባሽ አግሬ ጋሻና ጦር የሚሸከሙ ሦስት መቶ ሺህ የይሁዳ ሠራዊት፥ ጋሻም የሚሸከሙ ቀስትም የሚገትሩ ሁለት መቶ ሰማኒያ ሺህ የብንያም ሰዎች ነበሩት፤ እነዚህም ሁሉ ጽኑዓን ኃያላን ሰዎች ነበሩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለአሳም አላባሽ አግሬ ጋሻና ጦር የሚሸከሙ ሦስት መቶ ሺህ የይሁዳ ሠራዊት፥ ወንጭፍ የሚወነጭፉ፥ ቀስትም የሚገትሩ ሁለት መቶ ሰማንያ ሺህ የብንያም ሰዎች ነበሩት፤ እነዚህም ሁሉ ጽኑዓን ኀያላን ሰዎች ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለአሳም አላባሽ አግሬ ጋሻና ጦር የሚሸከሙ ሦስት መቶ ሺህ የይሁዳ ሠራዊት እና ጋሻ የሚሸከሙ፥ ቀስት የሚገትሩ ሁለት መቶ ሰማኒያ ሺህ የብንያም ሰዎች ነበሩት፤ እነዚህም ሁሉ ጽኑዓን ኃያላን ሰዎች ነበሩ። |
የኡላም ወንዶች ልጆች ዝነኛ ወታደሮችና ቀስት ወርዋሪዎች ነበሩ፤ የእነርሱም ዘሮች በአጠቃላይ አንድ መቶ ኀምሳ ልጆችና የልጅ ልጆች ነበሩ፤ እንግዲህ ከዚህ በላይ ስሞቻቸው የተጠቀሱት ሁሉ የብንያም ነገድ ነበሩ።
ንጉሥ ሮብዓም ወደ ኢየሩሳሌም በደረሰ ጊዜ ከይሁዳና ከብንያም ነገዶች የተውጣጡ አንድ መቶ ሰማኒያ ሺህ ምርጥ ወታደሮችን ጠርቶ በአንድነት ሰበሰበ፤ ይህንንም ያደረገበት ምክንያት የእስራኤልን ነገዶች ወግቶ ግዛቱን እንደገና በቊጥጥሩ ሥር ለማድረግ ዐቅዶ ስለ ነበር ነው።
ለእግዚአብሔር የነበራቸውን ታማኝነት በማጓደላቸውም ሮብዓም በነገሠ በአምስተኛው ዓመት የግብጽ ንጉሥ ሺሻቅ በኢየሩሳሌም ላይ አደጋ ጣለበት።
እርሱም አንድ ሺህ ሁለት መቶ ሠረገሎችና ሥልሳ ሺህ ፈረሰኞች ነበሩት፤ በሺሻቅ ጦር ሠራዊት ውስጥ ከእርሱ ጋር ከግብጽ የመጡ ብዛታቸው ሊቈጠር የማይቻል ሊቢያውያን፥ ሱካውያንና ኢትዮጵያውያን ነበሩ፤
ኢትዮጵያውያንና ሊቢያውያን ብዙ ሠራዊት፥ ሠረገሎችና ፈረሰኞች አልነበሩአቸውምን? ይሁን እንጂ በዚያን ጊዜ አንተ በእግዚአብሔር ስለ ታመንክ፥ እግዚአብሔር በእነርሱ ላይ ድልን እንድትቀዳጅ አደረገህ።
ንጉሥ አሜስያስ የይሁዳና የብንያም ነገዶች የሆኑትን ወንዶች ሁሉ በየጐሣዎቻቸው በቡድን በቡድን በመደልደል በየቡድኑ በሺህ አለቆችና በመቶ አለቆች ሥር መደበ፤ በቡድን የተመደቡትም ሰዎች ዕድሜአቸው ኻያ ዓመት ወይም ከዚያ በላይ የሆኑ ወንዶችን ሁሉ የሚያጠቃልል ሲሆን ብዛታቸውም ሦስት መቶ ሺህ ነበር፤ እነርሱም ለጦርነት የተዘጋጁ፥ በጦርና በጋሻ አያያዝ የሠለጠኑ ምርጥ ወታደሮች ነበሩ፤