ንጉሥ ሮብዓም ያደረገው ነገር ሁሉ ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ እንዲሁም የቤተሰቡ ታሪክ በነቢዩ ሸማዕያና በነቢዩ ዒዶ ታሪክ መጻሕፍት ተመዝግቦ ይገኛል፤ ሮብዓምና ኢዮርብዓም ባለማቋረጥ ዘወትር ይዋጉ ነበር፤
2 ዜና መዋዕል 13:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የቀረው የንጉሥ አቢያ ታሪክ፥ እርሱ የተናገራቸው ቃላትና ያከናወነው ሥራ ሁሉ፥ በነቢዩ ዒዶ የታሪክ መጽሐፍ ውስጥ ተመዝግቦ ይገኛል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በአብያ ዘመን የተከናወነው ተግባር፣ እርሱ የፈጸመውና የተናገረው ሁሉ በነቢዩ በአዶ የታሪክ መዛግብት ተጽፏል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የአብያም የቀረው ነገርና አካሄዱ የተናገራቸውም ቃሎች በነቢዩ በአዶ መጽሐፍ ተጽፈዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአብያም የቀረው ነገርና አካሄዱ የተናገራቸውም ቃሎች በነቢዩ በአዶ መጽሐፍ ተጽፈዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የአብያም የቀረው ነገርና አካሄዱ የተናገራቸውም ቃሎች በነቢዩ በአዶ መጽሐፍ ተጽፈዋል። |
ንጉሥ ሮብዓም ያደረገው ነገር ሁሉ ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ እንዲሁም የቤተሰቡ ታሪክ በነቢዩ ሸማዕያና በነቢዩ ዒዶ ታሪክ መጻሕፍት ተመዝግቦ ይገኛል፤ ሮብዓምና ኢዮርብዓም ባለማቋረጥ ዘወትር ይዋጉ ነበር፤
የኢዮአስ ልጆች ታሪክ፥ በኢዮአስ ላይ ተነግረው የነበሩት የትንቢት ቃላትና ኢዮአስ ቤተ መቅደሱን እንዴት እንዳደሰ በነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ መግለጫ ውስጥ ተመዝግቦ ይገኛል፤ በእርሱም እግር ተተክቶ ልጁ አሜስያስ ነገሠ።
ሌላው የሰሎሞን ታሪክ ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ በነቢዩ ናታን ታሪክ፥ የሴሎ ተወላጅ በሆነው በነቢዩ አኪያ ትንቢትና ስለ እስራኤል ንጉሥ ኢዮርብዓም ዘመነ መንግሥት ጭምር በሚናገረው በነቢዩ ዒዶ ራእይ ተመዝግቦ ይገኛል፤