2 ዜና መዋዕል 12:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሮብዓም ሞተ፤ በዳዊት ከተማ በሚገኘው በነገሥታት መካነ መቃብርም ተቀበረ፤ በእርሱም እግር ተተክቶ ልጁ አቢያ ነገሠ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሮብዓምም ከአባቶቹ ጋራ አንቀላፋ፤ በዳዊትም ከተማ ተቀበረ፤ ልጁ አብያም በርሱ ፈንታ ነገሠ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሮብዓምም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፥ በዳዊትም ከተማ ተቀበረ፤ ልጁም አብያ በእርሱ ፋንታ ነገሠ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሮብዓምም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በዳዊትም ከተማ ተቀበረ፤ ልጁም አብያ በእርሱ ፋንታ ነገሠ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሮብዓምም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በዳዊትም ከተማ ተቀበረ፤ ልጁም አብያ በእርሱ ፋንታ ነገሠ። |
ቈየት ብሎም ሮብዓም፥ ማዕካ ተብላ የምትጠራውን የአቤሴሎምን ልጅ አግብቶ አቢያ፥ ዓታይ፥ ዚዛና ሼሎሚት ተብለው የሚጠሩ አራት ወንዶች ልጆችን ወለደ።