2 ዜና መዋዕል 11:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህም የተነሣ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔርን በቅን መንፈስ ለማምለክ የፈለጉ ከመላው የእስራኤል ነገዶች የተውጣጡ ብዙ ሰዎች ለቀድሞ አባቶቻቸው አምላክ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት ለማቅረብ ሌዋውያኑን ተከትለው ወደ ኢየሩሳሌም መጡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከእያንዳንዱም የእስራኤል ነገድ ከልባቸው የእስራኤልን አምላክ እግዚአብሔርን የሚፈልጉ ሁሉ፣ ለአባቶቻቸው አምላክ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት ያቀርቡ ዘንድ፣ ሌዋውያኑን ተከትለው ወደ ኢየሩሳሌም ሄዱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ደግሞም ለአባቶቻቸው አምላክ ለጌታ ለመሠዋት ከእስራኤል ነገድ ሁሉ የእስራኤልን አምላክ ጌታን ለመፈለግ ልባቸውን የሰጡ ሁሉ እነርሱን ተከትለው ወደ ኢየሩሳሌም መጡ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ደግሞም ለአባቶቻቸው አምላክ ለእግዚአብሔር ይሠዉ ዘንድ ከእስራኤል ነገድ ሁሉ የእስራኤልን አምላክ እግዚአብሔርን ለመፈለግ ልባቸውን የሰጡ ሁሉ እነርሱን ተከትለው ወደ ኢየሩሳሌም መጡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ደግሞም ለአባቶቻቸው አምላክ ለእግዚአብሔር ይሠዉ ዘንድ ከእስራኤል ነገድ ሁሉ የእስራኤልን አምላክ እግዚአብሔርን ለመፈለግ ልባቸውን የሰጡ ሁሉ እነርሱን ተከትለው ወደ ኢየሩሳሌም መጡ። |
ዳዊትም “የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስና የእስራኤል ሕዝብ የሚቃጠል መሥዋዕት የሚያቀርቡበት መሠዊያ ሊኖሩ የሚገባቸው በዚህ ስፍራ ነው” አለ።
እንግዲህ አምላካችሁን እግዚአብሔርን በፍጹም ልባችሁና በፍጹም ነፍሳችሁ አገልግሉ፤ የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦትና እግዚአብሔርን ለማምለክ መገልገያ የሆኑትን ንዋያተ ቅድሳት ሁሉ አምጥታችሁ በውስጡ ማኖር ትችሉ ዘንድ ቤተ መቅደሱን ለክብሩ መሥራት ጀምሩ።”
ይህም ሁኔታ የይሁዳን መንግሥት አጠናከረ፤ ሦስት ዓመት ሙሉም የሰሎሞንን ልጅ ሮብዓምን ረዱ፤ የንጉሥ ዳዊትንና የንጉሥ ሰሎሞንን መንገድ ተከትለው በሰላም ኖሩ።
የይሁዳ ሰዎች ሁሉ በፍጹም ልባቸው ይህን ቃል ኪዳን ስለ ገቡ ደስ ተሰኝተው ነበር፤ እግዚአብሔርንም አጥብቀው ፈለጉት፤ እርሱም ተገኘላቸው፤ እግዚአብሔርም ከእነርሱ ጋር በመሆን በዙሪያቸው ሁሉ ሰላም እንዲኖር አደረገላቸው።
አምላኩ እግዚአብሔር ከንጉሥ አሳ ጋር መሆኑን ስላዩ፥ ከኤፍሬም፥ ከምናሴና ከስምዖን ነገዶች የሆኑ ብዙ ሰዎች ወደ አሳ መጥተው በግዛቱ ውስጥ ይኖሩ ነበር፤ አሳም እነዚህን ሰዎች ሁሉ፥ እንዲሁም መላው የይሁዳና የብንያም ሕዝብ ወደ ኢየሩሳሌም እንዲመጡ ትእዛዝ አስተላለፈ፤
ይህም ሁሉ ሆኖ አንዳንድ መልካም ነገር አድርገሃል፤ ይኸውም ሕዝቡ ያመልካት የነበረችውን አሼራ ተብላ የምትጠራውን ሴት አምላክ ምስሎችን ሁሉ ከምድሪቱ አስወግደሃል፤ የእግዚአብሔርንም ፈቃድ ለይተህ ለመፈጸም ጥረት አድርገሃል።”
ኢዮሣፍጥ እጅግ ስለ ፈራ ፈቃዱን እንዲገልጥለት ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፤ ከዚህ በኋላ በመላው አገሪቱ ሕዝቡ ሁሉ እንዲጾም ትእዛዝ አስተላለፈ፤
ይሁን እንጂ ለእግዚአብሔር ትሕትናን በማሳየት ወደ ኢየሩሳሌም ፈቃደኞች ሆነው የመጡ ከአሴር፥ ከምናሴና ከዛብሎን ነገዶች አንዳንድ ሰዎች ነበሩ፤
ንጉሡም ይህን በሰማ ጊዜ እጅግ አዘነ፤ ዳንኤልንም ለማዳን ወሰነ፤ ፀሐይም እስክትጠልቅ ድረስ እርሱን ለማዳን የሚችልበትን ዘዴ ሁሉ ለማግኘት ሞከረ።
እርሱም ሄዶ እግዚአብሔር ጸጋውን ለሕዝቡ እንዴት እንደ ሰጠ ባየ ጊዜ ደስ አለው፤ ሁሉም በሙሉ ልብ ጸንተው ለጌታ ታማኞች ሆነው እንዲኖሩም መከራቸው።
ከዚያም እኔ ያዘዝኳችሁን ነገር ሁሉ የምታመጡት እግዚአብሔር አምላካችሁ ለስሙ መጠሪያ ወደ መረጠው ቦታ ይሆናል፤ ይኸውም የሚቃጠል መሥዋዕታችሁንና ሌላውንም መሥዋዕታችሁን ሁሉ፥ ዐሥራታችሁንና መባችሁን ሁሉ፥ ለእግዚአብሔር የተሳላችሁትን የበጎ ፈቃድ ስጦታችሁን ሁሉ ታመጡለታላችሁ።
እርሱም እንዲህ አለ፦ “የዚህን ሕግ ቃላት በጥንቃቄ መጠበቅ ይችሉ ዘንድ ልጆቻችሁን እንድታዙ እኔ ዛሬ በእናንተ ላይ ምስክር እንዲሆን የምሰጣችሁን ቃላት ሁሉ አስተውሉ።
አሁን ግን ምድራችሁ የረከሰ ቢሆን የእግዚአብሔር ማደሪያ ወዳለበት ወደ እግዚአብሔር ምድር ተሻገሩ፤ በመካከላችን ርስት ይኑራችሁ፤ ነገር ግን ከእግዚአብሔር መሠዊያ ሌላ በመሥራት በእግዚአብሔር ላይ ወይም በእኛ ላይ አታምፁ።