2 ዜና መዋዕል 11:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሮብዓም እነዚህን ከተሞች አጠንክሮ መሸገ፤ ለእያንዳንዳቸውም አንዳንድ የከተማ ኀላፊ ሾመ፤ በእያንዳንዳቸውም ውስጥ እህል፥ የወይራ ዘይትና የወይን ጠጅ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነዚህንም ምሽጎቻቸውን አጠንክሮ፣ አዛዦችን ሾመባቸው፤ ምግብ፣ ዘይትና የወይን ጠጅ አከማቸባቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምሽጎቹንም አጠነከረ፥ አዛዦችንም አኖረባቸው፥ ምግቡንም ዘይቱንም የወይን ጠጁንም አከማቸባቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ምሽጎቹንም አጠነከረ፤ አለቆችንም አኖረባቸው፤ ምግቡንም፥ ዘይቱንም፥ የወይን ጠጁንም አከማቸባቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ምሽጎቹንም አጠነከረ፤ አለቆችንም አኖረባቸው፤ ምግቡን፥ ዘይቱን፥ የወይን ጠጁንም አከማቸባቸው። |
ሮብዓም ጥበብ በተሞላበት ሁናቴ ለወንዶች ልጆቹ ኀላፊነትን በመስጠት፥ በተመሸጉት የይሁዳና የብንያም ከተሞች ሁሉ ላይ ሾማቸው፤ የሚያስፈልጋቸውን ሁሉ በለጋሥነት አደራጀላቸው፤ ከብዙ ሚስቶችም ጋር አጋባቸው።
ስለዚህ ኢዮሣፍጥ ከጊዜ ወደ ጊዜ ይበልጥ ገናና እየሆነ ሄደ፤ በመላው ይሁዳ ምሽጎችንና፥ እጅግ የበዛ ስንቅና ትጥቅ የተከማቹባቸውን ከተማዎች ሠራ። በኢየሩሳሌምም የተለየ ችሎታ ያላቸውን ተዋጊዎች አኖረ፤
እነዚህ ሁሉ ወታደሮች ንጉሥ ኢዮሣፍጥን በኢየሩሳሌም የሚያገለግሉ ሲሆኑ፥ በተጨማሪም ንጉሡ በሌሎቹ በተመሸጉት የይሁዳ ከተሞች ሌሎች ወታደሮችን አስፍሮ ነበር።
“የሰው ልጅ ሆይ! አንድ በትር ወስደህ ‘በእርሱ ላይ ለይሁዳና ከእርሱ ጋር ለተባበሩ እስራኤላውያን’ ብለህ ጻፍ፤ ከዚያም ሌላ በትር ወስደህ በእርሱ ላይ ‘ለዮሴፍ ማለት ለኤፍሬምና ከእርሱ ጋር ለተባበሩ እስራኤላውያን’ ብለህ ጻፍ።