1 ተሰሎንቄ 5:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እናንተ ሁላችሁም የብርሃን ሰዎች፥ የቀንም ሰዎች ናችሁ፤ እኛ የሌሊት ወይም የጨለማ ሰዎች አይደለንም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሁላችሁም የብርሃን ልጆች፣ የቀንም ልጆች ናችሁና። እኛ ከሌሊት ወይም ከጨለማ ወገን አይደለንም፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እናንተ ሁላችሁም የብርሃን ልጆች፥ የቀንም ልጆች ናችሁና፤ ሆኖም እኛ ከሌሊት ወይም ከጨለማ አይደለንም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሁላችሁ የብርሃን ልጆች የቀንም ልጆች ናችሁና፤ እኛ ከሌሊት ወይም ከጨለማ አይደለንም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሁላችሁ የብርሃን ልጆች የቀንም ልጆች ናችሁና። እኛ ከሌሊት ወይም ከጨለማ አይደለንም፤ |
ጌታውም እምነት ያጐደለውን መጋቢ በብልኅነቱ አደነቀው፤ ይህም ከእግዚአብሔር ሰዎች ይልቅ የዓለም ሰዎች በዓለማዊ ኑሮአቸው ብልኆች መሆናቸውን ያሳያል።
ዐይናቸውን እንድትከፍትላቸውና ከጨለማ ወደ ብርሃን እንድታወጣቸው ከሰይጣንም ግዛት ወደ እግዚአብሔር እንድትመልሳቸው አደርግሃለሁ፤ እነርሱም በእኔ በማመናቸው ምክንያት የኃጢአታቸውን ይቅርታ ያገኛሉ፤ በተመረጡት መካከልም ርስትን ይካፈላሉ።’
እኛ ግን የብርሃን ሰዎች ስለ ሆንን ራስን በመግዛት በመጠን እንኑር፤ እምነትንና ፍቅርን እንደ ጥሩር እንልበስ፤ የመዳንን ተስፋ እንደ ራስ ቊር እንልበስ፤
ይሁን እንጂ በክርስቶስና በእናንተ ሕይወት ዘንድ እውነት ሆኖ የታየውን አዲስ ትእዛዝ እጽፍላችኋለሁ፤ ጨለማው ተወግዶ እውነተኛው ብርሃን አሁንም እያበራ ነው።