1 ተሰሎንቄ 4:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በጸጥታም ለመኖር እንድትጣጣሩ እና የራሳችሁን ጉዳይ እንድታስቡ ከዚህ በፊት እንዳዘዝናችሁም በገዛ እጃችሁ እንድትሠሩ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚህ በፊት እንዳዘዝናችሁ በገዛ እጃችሁ ሥሩ፤ በጸጥታ ኑሩ፤ በራሳችሁ ጕዳይ ላይ ብቻ አተኵሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በጸጥታ ለመኖር እንድትተጉ፥ በራሳችሁም ጉዳይ ላይ እንድታተኩሩ፥ እንዳዘዝናችሁም በራሳችሁ እጅ እንድትሰሩ እንለምናችኋለን፤ |
ይህም፥ ቤቱን ትቶ ወደ ሩቅ አገር የሄደውን ሰው ይመስላል፤ እርሱም እያንዳንዱን አገልጋይ በልዩ ልዩ የሥራ ኀላፊነት ላይ መደበ፤ ዘበኛውንም ተግቶ እንዲጠብቅ አዘዘው።
‘ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ የተባረከ ነው’ የሚለውን የጌታ ኢየሱስን ቃል በማስታወስ፥ በእጃችን እየሠራን ደካሞችን መርዳት እንደሚገባን በብዙ መንገድ አሳይቻችኋለሁ።”
እግዚአብሔርን በመፍራትና በመልካም ጠባይ እየተመራን በሰላምና በጸጥታ እንድንኖር በተለይ ለነገሥታትና በከፍተኛ ሥልጣን ላይ ላሉ ሁሉ ጸልዩ።
ደግሞም ሥራ መፍታትን ይማራሉ፤ ሥራ መፍታት ብቻ ሳይሆን በየሰዉ ቤት እየዞሩ ሰውን የሚያሙ፥ በሰው ነገር የሚገቡና መናገር የማይገባቸውን የሚናገሩ ይሆናሉ።
ነገር ግን ውበታችሁ በእግዚአብሔር ፊት ዋጋው እጅግ በከበረና በማይጠፋው ጌጥ በገርነትና በጭምትነት መንፈስ ያጌጠው፥ በልብ ተሰውሮ የሚገኘው፥ ውስጣዊ ሰውነት ይሁን።