ሁለቱም የሐሰት ምስክሮች ተነሥተው “ናቡቴ እግዚአብሔርንና ንጉሡን ሰድቦአል” ብለው በሕዝቡ ፊት በሐሰት መሰከሩበት፤ ስለዚህም ከከተማይቱ ውጪ በመውሰድ በድንጋይ ወግረው ገደሉት።
1 ነገሥት 21:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ናቡቴ ተወግሮ ተገድሎአል” የሚል መልእክትም ወደ ኤልዛቤል ላኩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ለኤልዛቤል፣ “ናቡቴ በድንጋይ ተወግሮ ሞቷል” ብለው ላኩባት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አክዓብም፦ “በማን?” አለ፥ እርሱም፦ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ‘በአውራጆቹ አለቆች ጉልማሶች’” አሉ፤ እርሱም፦ “ሰልፉን ማን ይጀምራል?” አለ፤ እርሱም፦ “አንተ” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አክዓብም፥ “በምን አውቃለሁ?” አለ፤ እርሱም፥ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በአውራጃዎቹ አለቆች ጐልማሶች” አለ፤ አክዓብም፥ “ውጊያውን ማን ይጀምራል?” አለ፤ እርሱም፥ “አንተ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አክዓብም፦ በማን? አለ፤ እርሱም፦ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በአውራጆቹ አለቆች ጕልማሶች አለ፤ እርሱም፦ ሰልፉን ማን ይጀምራል? አለ፤ እርሱም፦ አንተ አለው። |
ሁለቱም የሐሰት ምስክሮች ተነሥተው “ናቡቴ እግዚአብሔርንና ንጉሡን ሰድቦአል” ብለው በሕዝቡ ፊት በሐሰት መሰከሩበት፤ ስለዚህም ከከተማይቱ ውጪ በመውሰድ በድንጋይ ወግረው ገደሉት።
ኤልዛቤልም መልእክቱን እንደ ተቀበለች ወዲያውኑ አክዓብን “ናቡቴ ሞቶአል፤ በል አሁን ተነሥተህ ሂድና ለአንተ ለመሸጥ እምቢ ያለውን የወይን ተክል ቦታ ርስት አድርገህ ውሰድ” አለችው።
ኢዩ የአክዓብ ትውልድ ራሶች ተቈርጠው መምጣታቸውን በሰማ ጊዜ በከተማይቱ ቅጽር በር በሁለት ረድፍ ተከምረው እስከ ተከታዩ ቀን ጧት ድረስ እንዲቈዩ ትእዛዝ ሰጠ፤
በአንድ አገር ግፍ ሲሠራና መብት በመንፈግ ፍትሕ ሲጓደል ባየህ ጊዜ አትደነቅ፤ እያንዳንዱ ገዥ የበላይ ተመልካች አለው፤ ከሁሉም በላይ የሆነ ሌላ ተመልካች ደግሞ አለ።
በምድር ላይ የሚደረግ ከንቱ ነገር አለ፤ አንዳንድ ጊዜ ደጋግ ሰዎች ለክፉ ሰዎች የሚገባውን ቅጣት ይቀበላሉ፤ ክፉ ሰዎች ደግሞ ለደጋግ ሰዎች የሚገባውን ዋጋ ያገኛሉ፤ ይህም ሁሉ ከንቱ ነው አልኩ።