1 ነገሥት 15:27 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የይሳኮር ነገድ የሆነው የአኪያ ልጅ ባዕሻ በናዳብ ላይ ዐምፆ ገደለው፤ በዚያም ጊዜ ናዳብና ሠራዊቱ በፍልስጥኤም ግዛት የምትገኘውን የጊበቶንን ከተማ በመክበብ ላይ ነበሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ናዳብና መላው እስራኤል በፍልስጥኤም የምትገኘውን የገባቶንን ከተማ ከብበው ሳሉ፣ ከይሳኮር ነገድ የተወለደው የአኪያ ልጅ ባኦስ ዐምፆ በመነሣት ናዳብን በገባቶን ገደለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የይሳኮር ነገድ የሆነው የአኪያ ልጅ ባዕሻ በናዳብ ላይ ዐምፆ ገደለው፤ በዚያም ጊዜ ናዳብና ሠራዊቱ በፍልስጥኤም ግዛት የምትገኘውን የጊበቶንን ከተማ በመክበብ ላይ ነበሩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከበለዓን ቤት የሆነ የአኪያ ልጅ ባኦስ ዐመፀበት፤ ናባጥና እስራኤልም ሁሉ ገባቶንን ከብበው ነበርና ባኦስ በፍልስጥኤልም ሀገር ባለው በገባቶን ገደለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከይሳኮርም ቤት የሆነ የአኪያ ልጅ ባኦስ ተማማለበት፤ ናዳብና እስራኤልም ሁሉ ገባቶንን ከብበው ነበርና ባኦስ በፍልስጥኤም አገር ባለው በገባቶን ገደለው። |
በዚህን ጊዜ ዚምሪ ወደዚያ ቤት ሰተት ብሎ ገብቶ ኤላን ገደለው፤ እርሱም በኤላ እግር ተተክቶ ነገሠ፤ ይህም የሆነው የይሁዳ ንጉሥ አሳ በነገሠ በሃያ ሰባተኛው ዓመት ነበር።
አሳ በይሁዳ በነገሠ በሃያ ሰባተኛው ዓመት ዚምሪ በእስራኤል ላይ ነገሠ፤ መኖሪያውንም በቲርጻ አድርጎ በእስራኤል ላይ ሰባት ቀን ብቻ ነገሠ፤ በዚያን ጊዜ የእስራኤል ወታደሮች በፍልስጥኤም የምትገኘውን የጊበቶንን ከተማ ከበው ነበር።
እግዚአብሔር በነቢዩ ኢዩ አማካይነት በባዕሻና በቤተሰቡ ላይ ያን የትንቢት ቃል የተናገረበት ምክንያት፥ ባዕሻ በፈጸመው ኃጢአት እግዚአብሔርን ስላሳዘነ ነበር፤ ባዕሻ እግዚአብሔርን ያስቈጣውም ከእርሱ ፊት የነበረው ንጉሥ ባደረገው ዐይነት ስለ ሠራው ክፉ ነገር ብቻ ሳይሆን የኢዮርብዓምንም ቤተሰብ ሁሉ በመግደሉ ጭምር ነው።
የሠረገላዎቹ እኩሌታ ኀላፊ የሆነ ዚምሪ ተብሎ የሚጠራ ከጦር መኰንኖቹ አንዱ በንጉሡ ላይ ዐደመ፤ አንድ ቀን ኤላ በቲርጻ ከተማ የቤተ መንግሥቱ ኀላፊ በሆነው አርጻ ተብሎ በሚጠራው ባለሟሉ ቤት ብዙ መጠጥ ጠጥቶ ሰክሮ ነበር።
ከዚህ በኋላ የንጉሥ ኢዮአስ ባለሟሎች የሆኑ ባለሥልጣኖች አደሙበት፤ ከእነርሱም ሁለቱ የሺምዓት ልጅ ዮዛካርና የሾሜር ልጅ ይሆዛባድ ወደ ሲላ በሚወስደው ከኢየሩሳሌም በስተ ምሥራቅ በሚገኘው በተደለደለ መሬት ላይ በተሠራው ቤት ገደሉት፤ ኢዮአስም በዳዊት ከተማ በሚገኘው በነገሥታት መካነ መቃብር ተቀበረ፤ በእርሱም እግር ተተክቶ ልጁ አሜስያስ ነገሠ።
ከዚያም በኋላ የኢዮሣፍጥ ልጅ የኒምሺ ልጅ ኢዩ በንጉሥ ኢዮራም ላይ ሤራ ማካሄድ ጀመረ፤ ኢዮራም ከሶርያ ንጉሥ አዛሄል ጋር በራሞት በተደረገው ጦርነት ላይ ስለ ቈሰለ በዚያን ጊዜ በኢይዝራኤል ውስጥ በማገገም ላይ ነበር፤ ስለዚህም ኢዩ ጓደኞቹ የሆኑትን የጦር መኰንኖች “እናንተ በእርግጥ ከእኔ ጋር ከሆናችሁ በኢይዝራኤል የሚኖረውን ሕዝብ ለማስጠንቀቅ አንድ ወሬ ነጋሪ እንኳ ከራሞት ወጥቶ እንዳያመልጥ አድርጉ” አላቸው።
በብርቱም ቈስሎ ነበር፤ የጠላት ሠራዊት ከዚያ ተነሥቶ ከሄደ በኋላ ባለሟሎቹ ከሆኑት ባለሥልጣኖች የካህኑን የዮዳሄን ልጅ ደም ለመበቀል በንጉሡ ላይ አሢረው በአልጋው ላይ እንዳለ ገደሉት፤ ንጉሡም በዳዊት ከተማ ተቀበረ፤ ይሁን እንጂ በነገሥታት መካነ መቃብር አልተቀበረም።