ከዚህም በኋላ ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ አለ፤ “ስለዚህ ለሕወታችሁ ‘ምን እንበላለን? ለሰውነታችሁም ምን እንለብሳለን?’ በማለት ስለ ኑሮአችሁ አትጨነቁ እላችኋለሁ።
1 ቆሮንቶስ 7:33 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሚስት ያገባ ሰው ግን የሚያስበው ስለዚህ ዓለም ነገርና ሚስቱንም የሚያስደስትበትን ነገር ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ያገባ ሰው ግን ሚስቱን ደስ ለማሠኘት የዚህን ዓለም ነገር ያስባል፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ያገባው ግን ሚስቱን እንዴት ደስ እንደሚያሰኛት የዓለምን ነገር ያስባል፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያገባ ግን ሚስቱን ደስ ሊያሰኝ የዚህን ዓለም ኑሮ ያስባል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ያገባው ግን ሚስቱን እንዴት ደስ እንዲያሰኛት የዓለምን ነገር ያስባል፥ ልቡም ተከፍሎአል። |
ከዚህም በኋላ ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ አለ፤ “ስለዚህ ለሕወታችሁ ‘ምን እንበላለን? ለሰውነታችሁም ምን እንለብሳለን?’ በማለት ስለ ኑሮአችሁ አትጨነቁ እላችኋለሁ።
ስለዚህ በምንም ሐሳብ ሳትጨነቁ እንድትኖሩ እወዳለሁ፤ ሚስት ያላገባ ሰው ጌታ የሚደሰትበትን ነገር ስለሚፈልግ አሳቡ የሚያተኲረው፥ ጌታን በሚመለከት ሥራ ላይ ነው።
በዚህ ሁኔታ ሐሳቡ በሁለት ተከፍሎአል ማለት ነው። እንዲሁም ባል ያላገባች ሴት ወይም ልጃገረድ በሥጋዋና በነፍስዋ ተቀድሳ የጌታ ለመሆን ስለምትፈልግ ሐሳቧ የሚያተኲረው ጌታን በሚመለከት ሥራ ነው። ያገባች ሴት ግን ባልዋን ለማስደሰት ስለምትፈልግ የምታስበው የዓለምን ነገር ነው።
እናንተም ባሎች! ከሚስቶቻችሁ ጋር በማስተዋል አብራችሁ ኑሩ፤ ከእናንተ ይልቅ ደካማ ፍጥረት ስለ ሆኑና ከእናንተም ጋር የሕይወትን ጸጋ ስለሚወርሱ አክብሩአቸው፤ በዚህ ዐይነት ለጸሎታችሁ መሰናክል የሚሆን ነገር አይኖርም።