1 ቆሮንቶስ 16:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወንድሞች ሆይ! የእስጢፋኖስ ቤተሰብ በአካይያ አገር የመጀመሪያዎቹ አማኞች እንደ ሆኑና ምእመናንን ለማገልገል ራሳቸውን አሳልፈው እንደ ሰጡ ታውቃላችሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእስጢፋኖስ ቤተ ሰዎች በአካይያ የመጀመሪያዎቹ አማኞች እንደ ሆኑና ቅዱሳንንም ለማገልገል ራሳቸውን እንደ ሰጡ ታውቃላችሁ። ወንድሞች ሆይ፤ ይህን እለምናችኋለሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወንድሞች ሆይ፥ የእስጢፋኖስ ቤተሰቦች በአካይያ የመጀመሪያዎቹ አማኞች እንደሆኑና ቅዱሳንንም ለማገልገል ራሳቸውን እንደሰጡ ታውቃላችሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወንድሞቻችን ሆይ፥ የእስጢፋኖስና የፈርዶናጥስ፥ የአካይቆስም ቤተሰቦች፥ የአካይያ መጀመሪያዎች እንደ ሆኑ፥ ቅዱሳንንም ለማገልገል ራሳቸውን እንደ ሰጡ ታውቁ ዘንድ እማልዳችኋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወንድሞች ሆይ፥ የእስጢፋኖስ ቤተ ሰዎች የአካይያ በኩራት እንደ ሆኑ ቅዱሳንንም ለማገልገል ራሳቸውን እንደ ሰጡ ታውቃላችሁ፤ |
የምትጸልዩልኝም በይሁዳ ምድር ካሉት ከማያምኑ ሰዎች እጅ እንድድንና በኢየሩሳሌም ያለኝ አገልግሎትም በእግዚአብሔር ወገኖች ዘንድ ተቀባይነት እንዲኖረው ነው።
እርስዋ እኔንና ሌሎችንም ብዙ ሰዎች የረዳች ስለ ሆነች ምእመናን እንግዶችን መቀበል እንደሚገባቸው ዐይነት በጌታ ስም ተቀብላችሁ በሚያስፈልጋት ነገር ሁሉ እንድትረዱአት ዐደራ እላችኋለሁ።
በእነርሱ ቤት ለጸሎት ለሚሰበሰቡት ምእመናንም ሰላምታ አቅርቡልኝ። በእስያ ክፍለ ሀገር በመጀመሪያ በክርስቶስ ላመነውና ለምወደው ለኤጴኔጦስ ሰላምታ አቅርቡልኝ።
በእስጢፋኖስና በፈርዶናጥስ በአካይቆስም ወደ እኔ መምጣት ደስ ብሎኛል፤ እናንተ ከእኔ ጋር ባለመገኘታችሁ እነርሱ በእናንተ ምትክ የጐደለኝን አሟልተውልኛል።
እንዲሁም ልጆችን በሚገባ በማሳደግ፥ እንግዳን በመቀበል፥ የቅዱሳንን እግር በማጠብ፥ የተቸገሩትን በመርዳትና ማንኛውንም በጎ ሥራ ሁሉ በማከናወን ለመልካም ሥራም ሁሉ የተጋች መሆን አለባት።
እነርሱ ድንግሎች ስለ ሆኑ ከሴቶች ጋር ግንኙነት በማድረግ አልረከሱም፤ በጉ ወደሚሄድበትም ሁሉ ይከተሉታል። እነርሱ ለእግዚአብሔርና ለበጉ ከሰዎች መካከል እንደ በኲራት የቀረቡ ናቸው።