1 ቆሮንቶስ 14:39 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ወንድሞች ሆይ! ትንቢት ለመናገር በብርቱ ፈልጉ፤ በተለያዩ ቋንቋዎች መናገርንም አትከልክሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ፣ ወንድሞች ሆይ፤ ትንቢት ለመናገር በብርቱ ፈልጉ፤ በልሳን መናገርንም አትከልክሉ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ፥ ወንድሞች ሆይ፤ ትንቢት ለመናገር በብርቱ ፈልጉ፤ በልሳን መናገርንም አትከልክሉ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሁንም ወንድሞቻችን ሆይ፥ ትንቢትን ለመናገር ቅኑ፤ በቋንቋ የሚናገረውንም አትከልክሉት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህ ወንድሞች ሆይ፥ ትንቢት ለመናገር በብርቱ ፈልጉ፥ በልሳኖች ከመናገርም አትከልክሉ፤ |
ትንቢት የመናገር ስጦታ ቢኖረኝና ምሥጢርንም ሁሉ ብረዳ፥ ዕውቀትም ሁሉ ቢኖረኝ፥ ተራራን ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ የሚያፈልስ እምነትም ሁሉ ቢኖረኝ ፍቅር ከሌለኝ ከንቱ ነኝ።
ሁላችሁም በተለያዩ ቋንቋዎች ብትናገሩ እወድ ነበር፤ ይበልጥ የምወደው ግን ትንቢትን ብትናገሩ ነው፤ ማኅበረ ምእመናን እንዲታነጽ በተለያዩ ቋንቋዎች የተነገረውን የሚተረጒም ከሌለ፥ በተለያዩ ቋንቋዎች ከሚናገር ሰው ይልቅ ትንቢትን የሚናገር ሰው ይበልጣል።