1 ቆሮንቶስ 14:24 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን እያንዳንዱ የትንቢት ቃል ቢናገርና የማያምን ወይም የማያውቅ ሰው ቢመጣ በሚሰማው ቃል ሁሉ ይወቀሳል፤ እንዲሁም በሚሰማው ቃል ሁሉ ይፈረድበታል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን ሁሉም ትንቢት በመናገር ላይ ሳሉ፣ እንግዳ ወይም የማያምን ሰው ቢገባ፣ በሁሉ ይወቀሣል፤ በሁሉ ይመረመራል፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን ሁሉም ትንቢት በመናገር ላይ እያሉ፥ እንግዳ ወይም የማያምን ሰው ቢገባ፥ በሚሰማው ቃል ሁሉ ይወቀሳል፤ በሚሰማው ቃል ሁሉ ይመረመራል፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሁሉም ትንቢት ቢናገሩ ግን የማያምኑ ወይም አላዋቂዎች ቢመጡ ሁሉ ይከራከሩአቸው የለምን? ሁሉስ ያሳፍሩአቸው የለምን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሁሉ ትንቢት ቢናገሩ ግን የማያምን ወይም ያልተማረ ሰው ቢገባ በሁሉ ይወቀሳል፥ በሁሉም ይመረመራል፤ |
እንዲህማ ካልሆነ አንተ በመንፈስ እግዚአብሔርን ስታመሰግን፥ አንተ የምትለውን የማያውቅ እንግዳ ሰው ለምስጋና ጸሎትህ “አሜን” ሊል እንዴት ይችላል?