1 ዜና መዋዕል 7:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ብንያም ሦስት ወንዶች ልጆችን ወለደ፤ እነርሱም ቤላዕ፥ ቤኬርና ይዲዕኤል ተብለው የሚጠሩት ናቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሦስቱ የብንያም ወንዶች ልጆች፤ ቤላ፣ ቤኬር፣ ይዲኤል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የብንያም ልጆች ቤላ፥ ቤኬር፥ ይዲኤል ሦስት ነበሩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የብንያም ልጆች ቤላ፥ ቤኬር፥ ይድኤል ሦስት ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የብንያም ልጆች ቤላ፥ ቤኬር፥ ይዲኤል ሦስት ነበሩ። |
ቤላዕ አምስት ወንዶች ልጆችን ወለደ፤ እነርሱም ኤጽቦን፥ ዑዚ፥ ዑዚኤል፥ ያሪሞትና ዒሪ ተብለው የሚጠሩት ናቸው፤ እነርሱም በጐሣዎቻቸው ውስጥ የቤተሰብ አለቆችና ዝነኛ ወታደሮች ነበሩ፤ ከእነርሱ ተወላጆች መካከል ዕድሜአቸው ለውትድርና አገልግሎት የደረሰ ኻያ ሁለት ሺህ ሠላሳ አራት ወንዶች ነበሩ።