በሁሉም ነገር የተመቻቸና አስተማማኝ፥ ዘለዓለማዊ ቃል ኪዳን ከእኔ ጋር ስለ ገባ፥ በውኑ ቤቴ ለእግዚአብሔር ታማኝ አይደለም? ርዳታዬና ፍላጎቴስ ሁሉ እንዲሟላ አያደርግምን?
1 ዜና መዋዕል 7:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ኤፍሬም ከሚስቱ ጋር ግንኙነት አደረገ፤ እርስዋም ፀንሳ ወንድ ልጅ ወለደች፤ በቤተሰባቸው ላይ በደረሰው መከራ ምክንያት በሪዓ የሚል ስም አወጣለት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ወደ ሚስቱ ገብቶ ተኛ፤ እርሷም ፀነሰች፤ ወንድ ልጅም ወለደች፤ በቤተ ሰቡ ላይ ከደረሰው መከራ የተነሣ ስሙን በሪዓ አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኤፍሬምም ወደ ሚስቱ ገባ፥ አረገዘችም፥ ወንድ ልጅም ወለደች፤ በቤቱም መከራ ሆኖአልና ስሙ በሪዓ ብሎ ጠራው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ ሚስቱም ገባ፥ አረገዘችም፤ ወንድ ልጅም ወለደች፤ በቤቴም መከራ ሆኖአልና ሲል ስሙን በሪዓ ብሎ ጠራው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ ሚስቱም ገባ፤ አረገዘችም፤ ወንድ ልጅም ወለደች፤ በቤቱም መከራ ሆኖአልና ስሙን በሪዓ ብሎ ጠራው። |
በሁሉም ነገር የተመቻቸና አስተማማኝ፥ ዘለዓለማዊ ቃል ኪዳን ከእኔ ጋር ስለ ገባ፥ በውኑ ቤቴ ለእግዚአብሔር ታማኝ አይደለም? ርዳታዬና ፍላጎቴስ ሁሉ እንዲሟላ አያደርግምን?
ኤፍሬም፥ ሼኢራ ተብላ የምትጠራ ሴት ልጅ ወለደ፤ እርስዋም የላይኛውንና የታችኛውን ቤትሖሮን፥ እንዲሁም ዑዜንሼኢራ ተብለው የሚጠሩትን ከተማዎች አሠራች።