1 ዜና መዋዕል 7:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የማኪር ሚስት ማዕካ ፔሬሽና ሼሬሽ ተብለው የሚጠሩ ሁለት ወንዶች ልጆችን ወለደች፤ ጴሬሽ የሚል ስም ያወጣችለትም እርስዋ ናት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የማኪር ሚስት መዓካ ወንድ ልጅ ወለደች፤ ስሙንም ፋሬስ አለችው። የወንድሙም ስም ሱሮስ ይባላል፤ ወንዶች ልጆቹም ኡላምና ራቄም ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የማኪርም ሚስት መዓካ ልጅ ወለደች፥ ስሙንም ፋሬስ ብላ ጠራችው፤ የወንድሙም ስም ሱሮስ ነበረ፤ ልጆቹም ኡላም፥ ራቄም ነበሩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የማኪርም ሚስት መዓካ ልጅ ወለደች፥ ስሙንም ፋሬስ ብላ ጠራችው፤ የወንድሙም ስም ሱሮስ ነበረ፤ ልጆቹም ኡላምና ራቄም ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የማኪርም ሚስት መዓካ ልጅ ወለደች፤ ስሙንም ፋሬስ ብላ ጠራችው፤ የወንድሙም ስም ሱሮስ ነበረ፤ ልጆቹም ኡላምና ራቄም ነበሩ። |
ማኪር፥ ሑፊምና ሺፊም አንዳንድ ሴት እንዲያገቡ አደረገ፤ ማኪር ማዕካ ተብላ የምትጠራ እኅት ነበረችው፤ ጸሎፍሐድ ተብሎ የሚጠራው የማኪር ሁለተኛ ልጅ ሴቶች ልጆችን ብቻ ወለደ።