ይስሐቅ የባቱኤልን ልጅ ርብቃን ሲያገባ አርባ ዓመት ሆኖት ነበር፤ የርብቃ አባት ባቱኤልና ወንድምዋ ላባ በመስጴጦምያ የሚኖሩ ሶርያውያን ነበሩ፤
1 ዜና መዋዕል 7:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ምናሴ ከሶርያዊት ቊባቱ አስሪኤልና ማኪር ተብለው የሚጠሩ ሁለት ወንዶች ልጆችን ወለደ፤ ማኪርም ገለዓድን ወለደ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የምናሴ ዘሮች፤ ሶርያዊት ቁባቱ የወለደችለት ልጁ አሥሪኤል ነው። እርሷም የገለዓድን አባት ማኪርን የወለደች ናት፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የምናሴ ልጆች ሶርያይቱ ቁባቱ የወለደችለት እስርኤልና የገለዓድ አባት ማኪር ናቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የምናሴ ልጆች ሶሪያዪቱ ቁባቱ የወለደችለት አስርኤልና የገለዓድ አባት ማኪር ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የምናሴ ልጆች ሶርያይቱ ቁባቱ የወለደችለት እስርኤልና የገለዓድ አባት ማኪር ናቸው። |
ይስሐቅ የባቱኤልን ልጅ ርብቃን ሲያገባ አርባ ዓመት ሆኖት ነበር፤ የርብቃ አባት ባቱኤልና ወንድምዋ ላባ በመስጴጦምያ የሚኖሩ ሶርያውያን ነበሩ፤
ማኪር፥ ሑፊምና ሺፊም አንዳንድ ሴት እንዲያገቡ አደረገ፤ ማኪር ማዕካ ተብላ የምትጠራ እኅት ነበረችው፤ ጸሎፍሐድ ተብሎ የሚጠራው የማኪር ሁለተኛ ልጅ ሴቶች ልጆችን ብቻ ወለደ።
የሔፌር፥ የገለዓድ፥ የማኪር፥ የምናሴ፥ የዮሴፍ ልጅ የሆነው ጸሎፍሐድ፥ ማሕላ፥ ኖዓ፥ ሖግላ፥ ሚልካ እና ቲርጻ ተብለው የሚጠሩ ሴቶች ልጆች ነበሩት።
እንዲሁም የገለዓድ እኩሌታ፥ አስታሮት እና ኤድራይ እነርሱም በባሳን የንጉሥ ዖግ ከተሞች የነበሩት ይህም ከምናሴ ነገድ ለእኩሌቶቹ የማኪር ልጆች እንደየወገናቸው ተከፋፈሉት።
ቀድሞ ዐማሌቃውያን ይኖሩበት ከነበረው ከኤፍሬም ወታደሮች መጡ፤ ሌሎችም ከብንያም መጡ። ከማኪር መሪዎች፥ ከዛብሎንም በትረ መንግሥትን የሚይዙ መጡ።