የጋድ ነገድ፥ የሮቤል ነገድ ከሚኖሩበት በስተ ሰሜን ባለው ምድር ይኖሩ ነበር፤ ይህም ምድር በባሳን ውስጥ ሲሆን በስተ ምሥራቅ እስከ ሳለካ ይደርሳል።
1 ዜና መዋዕል 5:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢዩኤል ከሁሉ ለሚበልጠው ጐሣ አባት ሲሆን፥ ሻፋም ደግሞ በሁለተኛ ደረጃ ለሚገኘው ጐሣ አባት ነው፤ ያዕናይና ሻፋጥ በበሳን ይኖሩ ለነበሩት ለሌሎች ጐሣዎች አባቶች ነበሩ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም አለቃው ኢዮኤል፣ ሁለተኛው ሳፋም ከዚያም ያናይና ሰፋጥ ሆነው በባሳን ተቀመጡ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንደኛው ኢዮኤል፥ ሁለተኛው ሳፋም፥ ያናይ፥ ሳፋጥ በባሳን ተቀመጡ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በኵሩ ኢዩኤል፥ ሁለተኛው ሳፋም፥ ጸሓፊው ያናይን፥ ሳፋጥም በባሳን ተቀመጡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንደኛው ኢዮኤል፥ ሁለተኛው ሳፋም፥ ያናይ፥ ሳፋጥ በበሳን ተቀመጡ። |
የጋድ ነገድ፥ የሮቤል ነገድ ከሚኖሩበት በስተ ሰሜን ባለው ምድር ይኖሩ ነበር፤ ይህም ምድር በባሳን ውስጥ ሲሆን በስተ ምሥራቅ እስከ ሳለካ ይደርሳል።