እግዚአብሔርም፥ “በማሕፀንሽ ያሉት ሁለት ሕዝቦች ናቸው፤ እርስ በርሳቸው የማይስማሙ ሁለት ወገኖች ትወልጃለሽ፤ አንዱም ከሌላው የበረታ ይሆናል፤ ታላቁም ለታናሹ አገልጋይ ይሆናል” አላት።
1 ዜና መዋዕል 5:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የያዕቆብ የበኲር ልጅ የሆነው የሮቤል ዘሮች ቀጥሎ የተመለከቱት ናቸው፤ (ሮቤል የአባቱን አልጋ ደፍሮ በማርከሱ የብኲርናውን መብት ስላጣ፥ ያ መብት ለዮሴፍ ተሰጥቶ ነበር፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእስራኤል የበኵር ልጅ የሮቤል ልጆች፤ ሮቤል የበኵር ልጅ ቢሆንም፣ የአባቱን መኝታ ስላረከሰ፣ የብኵርና መብቱ ለእስራኤል ልጅ ለዮሴፍ ልጆች ተሰጥቷል። ከዚህም የተነሣ ትውልዱ የበኵርነቱን ተራ ይዞ ሊቈጠር አልቻለም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእስራኤልም በኩር የሮቤል ልጆች እነዚህ ናቸው። እርሱ የበኩር ልጅ ነበረ፤ ነገር ግን የአባቱን ምንጣፍ ስላረከሰ ብኩርናው ለእስራኤል ልጅ ለዮሴፍ ልጆች ተሰጠ፤ ትውልዱ ግን ከብኩርናው ጋር አልተቈጠረም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእስራኤልም በኵር የሮቤል ልጆች እነዚህ ናቸው። እርሱ የበኵር ልጅ ነበረ፤ ነገር ግን ወደ አባቱ ምንጣፍ ስለ ወጣ አባቱ እስራኤል በረከቱን ለልጁ ለዮሴፍ ሰጠ፤ ብኵርናም አልተቈጠረለትም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእስራኤልም በኵር የሮቤል ልጆች እነዚህ ናቸው። እርሱ የበኵር ልጅ ነበረ፤ ነገር ግን የአባቱን ምንጣፍ ስላረከሰ ብኵርናው ለእስራኤል ልጅ ለዮሴፍ ልጆች ተሰጠ፤ ትውልዱ ግን ከብኵርና ጋር አልተቈጠረም። |
እግዚአብሔርም፥ “በማሕፀንሽ ያሉት ሁለት ሕዝቦች ናቸው፤ እርስ በርሳቸው የማይስማሙ ሁለት ወገኖች ትወልጃለሽ፤ አንዱም ከሌላው የበረታ ይሆናል፤ ታላቁም ለታናሹ አገልጋይ ይሆናል” አላት።
ያዕቆብ በዚያ ምድር ሲኖር ሳለ፥ ሮቤል ወደ አባቱ ቁባት ወደ ባላ ገባ። ያዕቆብም ይህን ነገር ሰማ። የያዕቆብ ወንዶች ልጆች ዐሥራ ሁለት ናቸው።
ያዕቆብ ንግግሩን በመቀጠል እንዲህ አለ፤ “ልጄ ዮሴፍ እኔ እዚህ ከመምጣቴ በፊት በግብጽ ምድር የተወለዱልህ ሁለት ልጆችህ ከእንግዲህ የእኔ ልጆች ናቸው፤ ኤፍሬምና ምናሴ እንደ ሮቤልና እንደ ስምዖን ይቈጠራሉ።
ከመራሪ ጐሣ አራት ወንዶች ልጆች የነበሩት ሖሳ ተብሎ የሚጠራ ሰው ነበር፤ ልጆቹም፥ ምንም እንኳ የበኲር ልጅ ባይሆንም አባቱ መሪ ያደረገው ሺምሪ፥
የያዕቆብ በኲር ልጅ ሮቤል፥ ሐኖክ፥ ፋሉ፥ ሔጽሮንና ካርሚ የሚባሉ ወንዶች ልጆች ነበሩት፤ እነዚህም በየስማቸው የሮቤል ነገድ አባቶች ናቸው።
አንድ ሰው የአባቱ ሚስት ከሆነችው ሴት ጋር ቢተኛ፥ የአባቱን ኀፍረተ ሥጋ ስለ ገለጠ እርሱና ሴትዮዋ ሁለቱም በሞት ይቀጡ፤ የተፈረደባቸውም በራሳቸው በደል ነው።
በመካከላችሁ አሳፋሪ የዝሙት ሥራ መኖሩ ይወራል፤ እንዲህ ዐይነቱ የዝሙት ሥራ በአሕዛብ ዘንድ እንኳ የማይደረግ ነው፤ ይኸውም የእንጀራ እናቱን እንደ ሚስት አድርጎ የሚኖር አለ ተብሎአል።
ከማያፈቅራት ሚስቱ የተወለደ ቢሆንም እንኳ ለበኲር ልጁ የሚሰጠው ድርሻ ከሌሎቹ የነፍስ ወከፍ ድርሻ በእጥፍ ከፍ ያለ መሆን አለበት፤ ስለዚህም ያ ሰው ልጁ በመጀመሪያ በመወለዱ በኲር መሆኑን ተረድቶ የብኲርና ድርሻውን ሊሰጠው ይገባል።
“ ‘የአባቱ ሚስቶች ከሆኑት ከየትኛዋም ጋር ግንኙነት በማድረግ የአባቱን ክብር የሚያዋርድ ሁሉ የተረገመ ይሁን!’ “ሕዝቡም ሁሉ ‘አሜን!’ ይበሉ።
የዮሴፍ ግርማ እንደ ኰርማ አስፈሪ ነው፤ ቀንዶቹም እንደ ጐሽ ቀንዶች ጠንካሮች ናቸው፤ በእነርሱም ሕዝቦችን ይወጋል፤ እስከ ምድር ዳርቻም ያባርራል፤ የኤፍሬም ዐሥር ሺሆች የምናሴም ሺሆች እንደዚያው ናቸው።”
አንድ ቀን ከይሁዳ ነገድ የሆኑ ሰዎች በጌልገላ ወደ ኢያሱ ቀረቡ፤ ከእነርሱ አንዱ የቀኒዛዊው የይፉኔ ልጅ ካሌብ እንዲህ አለው፦ “በቃዴስ በርኔ በነበርንበት ጊዜ እግዚአብሔር በአገልጋዩ በሙሴ አማካይነት ስለ አንተና ስለ እኔ የተናገረውን ታውቃለህ፤