1 ዜና መዋዕል 4:41 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በይሁዳ ንጉሥ በሕዝቅያስ ዘመነ መንግሥት ከላይ የተጠቀሱት ሰዎች ወደ ገራር ሄደው በዚያ የሚኖሩትን ሰዎች ድንኳንና ጎጆ ሁሉ አፈራረሱ፤ የካምን ነገዶችና መዑናውያንንም ፈጽመው ፈጁአቸው ለበጎቻቸው ብዙ የግጦሽ ቦታ ስላገኙም ሕዝቡን አባረው ለዘለቄታው እዚያው መኖር ጀመሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነዚህ ስማቸው ከላይ የተዘረዘረው ወደዚህ ቦታ የመጡት በይሁዳ ንጉሥ በሕዝቅያስ ዘመን ነበረ፤ እነርሱም በድንኳኖቻቸው ውስጥ በነበሩት በካም ወገኖችና በምዑናውያን ላይ አደጋ በመጣል ፈጽመው አጠፏቸው፤ ይህም እስከ ዛሬ ድረስ በግልጽ ይታያል። ለመንጎቻቸው በቂ የግጦሽ ቦታ ስላገኙም፣ በዚያ መኖር ጀመሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነዚህም በስማቸው የተጻፉ በይሁዳ ንጉሥ በሕዝቅያስ ዘመን መጥተው ድንኳኖቻቸውንና በዚያ የተገኙትን ምዑናውያንን መቱ፥ እስከ ዛሬም ድረስ ፈጽመው አጠፉአቸው፤ በዚያም ለመንጎቻቸው መሰማሪያ ነበረና በስፍራቸው ተቀመጡ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በስማቸው የተጻፉ እነዚህም በይሁዳ ንጉሥ በሕዝቅያስ ዘመን መጥተው ድንኳኖቻቸውንና በዚያ የተገኙትን ምዑናውያንን መቱ፥ እስከ ዛሬም ድረስ ፈጽመው አጠፉአቸው፤ በዚያም ለመንጎቻቸው መሰማሪያ ነበርና በስፍራቸው ተቀመጡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነዚህም በስማቸው የተጻፉ በይሁዳ ንጉሥ በሕዝቅያስ ዘመን መጥተው ድንኳኖቻቸውንና በዚያ የተገኙትን ምዑናውያንን መቱ፤ እስከ ዛሬም ድረስ ፈጽመው አጠፉአቸው፤ በዚያም ለመንጎቻቸው መሰማርያ ነበረና በስፍራቸው ተቀመጡ። |
በአካባቢያቸው በሚገኙ መንደሮች ይኖሩ ነበር፤ ይህም እነርሱ የሚኖሩበት ስፍራ እስከ ባዕላት ከተማ ይዘልቅ ነበር። እንግዲህ የስምዖን ዘሮች ስለ ቤተሰቦቻቸውና ስለሚኖሩባቸው ስፍራዎች መዝግበው ያቈዩት ጽሑፍ ይህ ነበር።
ጦርነቱ እግዚአብሔር የፈቀደው ስለ ነበረ፥ ከጠላት ወገን ብዙ ሰዎችን ገደሉ፤ እነርሱም ራሳቸው ተማርከው እስከ ተወሰዱበት ጊዜ ድረስ በምድሪቱ ላይ መኖራቸውን ቀጠሉ።
እንዲሁም በአንዳንድ እረኞች ሰፈር ላይ አደጋ በመጣል ብዙ በጎችን፥ ፍየሎችንና ግመሎችን ማረኩ፤ ከዚህም በኋላ ወደ ኢየሩሳሌም ተመልሰው ሄዱ።
ስለዚህም በኤዶም ሕዝብ ላይ ያቀድኩትንና በቴማን ከተማ ሕዝብ ላይ ላደርግ የፈለግኹትን ስሙ፤ ልጆቻቸው እንኳ እንደ በግ ግልገሎች እየተጐተቱ ይወሰዳሉ፤ በእነርሱም ምክንያት የሚያያቸው ሁሉ ይደነግጣል።
እርሱ የሰውን ዘር ሁሉ ከአንድ ሰው ፈጠረ፤ በምድር ሁሉ ላይ እንዲኖሩም አደረገ፤ የተወሰኑ ዘመኖችንና የሚኖሩባቸውንም ቦታዎች መደበላቸው።