1 ዜና መዋዕል 23:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዕድሜአቸው ሠላሳና ከዚያም በላይ የሆኑትን ሌዋውያን ወንዶችን ቈጠረ፤ ጠቅላላ ድምራቸውም ሠላሳ ስምንት ሺህ ሆነ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዕድሜያቸው ሠላሳና ከዚያ በላይ የሆኑ ወንዶች ሁሉ ተቈጠሩ፤ ቍጥራቸውም በጠቅላላው ሠላሳ ስምንት ሺሕ ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሌዋውያንም ዕድሜአቸው ሠላሳ ዓመትና ከዚያ በላይ የሆኑት ተቈጠሩ፤ በእያንዳንዳንዱ ነፍስ ወከፍ ተቈጠሩ፤ ድምራቸውም ሠላሳ ስምንት ሺህ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሌዋውያንም ከሠላሳ ዓመት ዕድሜ ጀምሮ ወደ ላይ ተቈጠሩ፤ ቍጥራቸውም በእያንዳንዱ ነፍስ ወከፍ ሲቈጠሩ ሠላሳ ስምንት ሺህ ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሌዋውያንም ከሠላሳ ዓመት ዕድሜ ጀምሮ ወደ ላይ ተቈጠሩ፤ ቍጥራቸው በእያንዳንዳንዱ ነፍስ ወከፍ ሠላሳ ስምንት ሺህ ነበር። |
እንግዲህ እነዚህ ሁሉ በየጐሣቸውና በየቤተሰባቸው የተዘረዘሩት የሌዊ ዘሮች ሲሆኑ፥ እያንዳንዳቸው በየስማቸው ተጠቅሰዋል። ኻያ ዓመት የሞላው ወይም ከዚያ በላይ የሆነው እያንዳንዱ የሌዊ ዘር በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ውስጥ ባለው ሥራ ድርሻ ነበረው።
በተጨማሪም በተለያዩ የየዕለት ተግባራቸው ወደ ቤተ መቅደስ ለሚገቡ ከሦስት ዓመት ዕድሜ በላይ ላላቸው ወንዶች እንደየ ኀላፊነታቸውና እንደየምድባቸው ድርሻ ድርሻቸውን ያከፋፍሉ ነበር፤