ወደ ንጉሥ ዳዊት ገብተሽ ‘ልጅሽ ሰሎሞን ከእኔ በኋላ ነግሦ በዙፋኔ ይቀመጣል’ ብለህ ለአገልጋይህ በመሐላ ቃል ገብተህልኝ አልነበረምን? ታዲያ፥ አሁን አዶንያስ እንዴት ሊነግሥ ቻለ? ብለሽ ንገሪው”።
1 ዜና መዋዕል 22:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይሁን እንጂ እንዲህ በማለት የተስፋ ቃል ሰጥቶኛል፥ ‘እኔ ከጠላቶቹ ሁሉ አሳርፌ ሰላም ስለምሰጠው በሰላም የሚያስተዳድር ወንድ ልጅ ይኖርሃል፤ በእርሱ ዘመነ መንግሥት ለእስራኤል ሰላምና ጸጥታ ስለምሰጥ ስሙ ሰሎሞን ተብሎ ይጠራል፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን የሰላምና የዕረፍት ሰው የሆነ ልጅ ትወልዳለህ፤ በየአቅጣጫው ካሉ ጠላቶቹ አሳርፈዋለሁ፤ ስሙም ሰሎሞን ይባላል። በዘመኑም ለእስራኤል ሰላምንና ጸጥታን እሰጣለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነሆ፥ ልጅ ይወለድልሃል፤ እርሱም ሰላም ያለው ሰው ይሆናል፤ በዙሪያው ካሉ ከጠላቶቹ ሁሉ አሳርፈዋለሁ፤ ስሙ ሰሎሞን ይባላልና፥ በዘመኑም ሰላምና ጸጥታን ለእስራኤል እሰጣለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነሆ፥ ልጅ ይወለድልሃል፤ የዕረፍት ሰውም ይሆናል፤ በዙሪያውም ካሉ ከጠላቶቹ ሁሉ አሳርፈዋለሁ፤ ስሙ ሰሎሞን ይባላልና፥ በዘመኑም ሰላምንና ጸጥታን ለእስራኤል እሰጣለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነሆ፥ የዕረፍት ሰው የሚሆን ልጅ ይወለድልሃል፤ በዙሪያው ካሉ ከጠላቶቹ ሁሉ አሳርፈዋለሁ፤ ስሙ ሰሎሞን ይባላልና፤ በዘመኑም ሰላምና ጸጥታን ለእስራኤል እሰጣለሁ። |
ወደ ንጉሥ ዳዊት ገብተሽ ‘ልጅሽ ሰሎሞን ከእኔ በኋላ ነግሦ በዙፋኔ ይቀመጣል’ ብለህ ለአገልጋይህ በመሐላ ቃል ገብተህልኝ አልነበረምን? ታዲያ፥ አሁን አዶንያስ እንዴት ሊነግሥ ቻለ? ብለሽ ንገሪው”።
አዶንያስም እንዲህ አላት፦ “ንጉሥ መሆን የሚገባኝ እኔ እንደ ነበርኩና ይህንንም በእስራኤል ምድር የሚኖር ሁሉ በተስፋ ይጠባበቅ እንደ ነበር አንቺ ራስሽ ታውቂያለሽ፤ ነገር ግን ጉዳዩ ከእግዚአብሔር ስለ ተወሰነ ለእኔ መሰጠት የሚገባው መንግሥት ተላልፎ ለወንድሜ ሆኖአል።
እግዚአብሔር አምላክ ሆይ! እነሆ እኔ በዕድሜ አነስተኛ ነኝ፤ የአመራር ልምድም የለኝም፤ አንተ ግን በአባቴ እግር ተተክቼ እንድነግሥ ፈቃድህ ሆኖአል፤
ሰሎሞን ከኤፍራጥስ ወንዝ በስተ ምዕራብ ያለውን ምድር ሁሉ ከቲፍሳሕ ከተማ ጀምሮ እስከ ጋዛ ከተማ ድረስ ይገዛ ነበር፤ ይህም ከኤፍራጥስ ወንዝ በስተ ምዕራብ የሚገኙትን ነገሥታት ሁሉ ያጠቃልላል፤ ጐረቤቱ ከሆኑት አገሮችም ሁሉ ጋር በሰላም ይኖር ነበር።
በኖረበትም ዘመን ሁሉ ከዳን እስከ ቤርሳቤህ ድረስ መላው የይሁዳና የእስራኤል ሕዝብ ያለስጋት በሰላም ይኖር ነበር፤ እያንዳንዱ ቤተሰብ የራሱ የሆነ የወይን ተክልና የበለስ ዛፍ ስለ ነበረው በእነዚህ ተክሎች ጥላ ሥር ያርፍ ነበር።
“በገባው የተስፋ ቃል መሠረት ለሕዝቡ ሰላምን የሰጠ እግዚአብሔር ይመስገን፤ በአገልጋዩ በሙሴ አማካይነት ከሰጠውም መልካም ተስፋ ምንም የቀረ የለም።
“አምላካችሁ እግዚአብሔር እስከ አሁን ከእናንተ ጋር አይደለምን? በሁሉም አቅጣጫ ሰላምን ሰጥቶአችሁ የለምን? በዚህች ምድር ላይ ይኖሩ የነበሩትን ሕዝቦች ሁሉ ድል አድርጌ እንድይዛቸው ፈቅዶልኛል፤ እነርሱም ለእናንተና ለእግዚአብሔር ተገዢዎች ሆነዋል፤
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ሀብትዋን እንደ ወንዝ ውሃ አበዛዋለሁ፤ የሕዝቦችንም ሀብት እንደ ወንዝ ጅረት አደርገዋለሁ፤ በክንድዋም ተይዛችሁ ትጠባላችሁ፤ በጭንዋም ላይ አድርጋ ትንከባከባችኋለች።
አዲሱ ቤተ መቅደስ ከፊተኛው ይበልጥ የተዋበ ይሆናል፤ እኔም በዚያ ለሕዝቤ የተሟላ ሰላምን እሰጣለሁ፤” የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ይህን ተናግሮአል።
ጌዴዎንም በዚያ መሠዊያ ሠርቶ “እግዚአብሔር የሰላም አምላክ ነው” ብሎ ሰየመው፤ (ይህም መሠዊያ እስከ ዛሬ የአቢዔዜር ጐሣ ይዞታ በሆነችው በዖፍራ ቆሞ ይገኛል።)