የጢሮስ ንጉሥ ኪራም ለዳዊት ቤተ መንግሥት ይሠሩለት ዘንድ አናጢዎች፥ ግንበኞችና የሊባኖስ ዛፍ እንጨት አስይዞ መልእክተኞችን ወደ ዳዊት ላከ።
1 ዜና መዋዕል 22:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሥ ዳዊት በእስራኤል ምድር የሚኖሩትን መጻተኞች በአንድነት ሰብስቦ በሥራ ላይ እንዲሰማሩ አደረገ፤ ከእነርሱ አንዳንዶቹ ለቤተ መቅደሱ መሥሪያ እንዲሆን ድንጋይ ጠራቢዎችን መደበ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ዳዊት በእስራኤል የሚኖሩ መጻተኞች እንዲሰበሰቡ አዘዘ፤ ከመካከላቸውም የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ የሚሠራበትን ጥርብ ድንጋይ እንዲያዘጋጁ ጠራቢዎችን መደበ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዳዊትም በእስራኤል ምድር የነበሩትን መጻተኞች እንዲሰበስቡ አዘዘ፤ የእግዚአብሔርንም ቤት ለመሥራት የሚወቀሩትን ድንጋዮች እንዲወቅሩ ጠራቢዎችን አኖረ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊትም በእስራኤል ምድር የነበሩትን መጻተኞች ይሰበስቡ ዘንድ አዘዘ፤ የእግዚአብሔርንም ቤት ለመሥራት የሚወቀሩትን ድንጋዮች ይወቅሩ ዘንድ ጠራቢዎችን አኖረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳዊትም በእስራኤል ምድር የነበሩትን መጻተኞች ይሰበስቡ ዘንድ አዘዘ፤ የእግዚአብሔርንም ቤት ለመሥራት የሚወቀሩትን ድንጋዮች ይወቅሩ ዘንድ ጠራቢዎችን አኖረ። |
የጢሮስ ንጉሥ ኪራም ለዳዊት ቤተ መንግሥት ይሠሩለት ዘንድ አናጢዎች፥ ግንበኞችና የሊባኖስ ዛፍ እንጨት አስይዞ መልእክተኞችን ወደ ዳዊት ላከ።
ቤተ መቅደሱ የታነጸባቸው ድንጋዮች ተጠርበው የተዘጋጁት፤ በዚያው በተፈለጡበት ቦታ ነበር፤ ስለዚህም ቤተ መቅደሱ በሚሠራበት ጊዜ የመዶሻ፥ የመጥረቢያ ወይም የሌላ ብረት ነክ መሣሪያ ድምፅ አይሰማም ነበር።
ለድንጋይ ጠራቢዎች፥ ለማደሻ አገልግሎት የሚውል እንጨትና ድንጋይ ለሚገዙና እንዲሁም ለልዩ ልዩ አስፈላጊ ነገሮች ለሚውል ተግባር ሁሉ ይከፍሉ ነበር።
የጢሮስ ንጉሥ ኪራም መልእክተኞችን ወደ ዳዊት ላከ፤ ከእነርሱም ጋር ለዳዊት ቤተ መንግሥት የሚሠሩለት የሊባኖስ ዛፍ ግንድ የያዙ አናጢዎችና ግንበኞች ነበሩ፤
ንጉሥ ዳዊት ለመላው ጉባኤ እንዲህ ሲል አስታወቀ፤ “እነሆ እግዚአብሔር የመረጠው ልጄ ሰሎሞን ገና ወጣትና የሥራ ልምድ የሌለው ነው፤ ይህ የሚሠራው ቤት፥ ቤተ መንግሥት ሳይሆን እግዚአብሔር አምላካችን የሚመለክበት ቤተ መቅደስ ስለ ሆነ መከናወን ያለበት ሥራ እጅግ ከባድ ነው።
እኛም የምትፈልገውን ግንድ ሁሉ ከሊባኖስ ተራራዎች ቈርጠን አንድ ላይ በማሰር በባሕር ላይ ተንሳፍፎ እስከ ኢዮጴ እንዲደርስ እናደርጋለን፤ ከዚያም ወደ ኢየሩሳሌም ልትወስደው ትችላለህ።”
ንጉሥ ሰሎሞን ከዚህ በፊት አባቱ ዳዊት ባደረገው ዐይነት በእስራኤል ምድር የሚኖሩትን የውጪ አገር ሰዎች ቈጠረ፤ በዚህም ዐይነት በግዛቱ ውስጥ አንድ መቶ ኀምሳ ሦስት ሺህ ስድስት መቶ መጻተኞች መኖራቸው ተረጋገጠ፤
እንዲሁም ሕዝቡ ለግንበኞችና ለአናጢዎች የሚከፈለውን ገንዘብ ሰጡ፤ ከሊባኖስ ዛፍ ቈርጠው በኢዮጴ የባሕር ጠረፍ በኩል እንዲልኩላቸው ለጢሮስና ለሲዶና ከተሞች ነዋሪዎች ምግብን፥ መጠጥንና የወይራ ዘይትን ላኩ፤ ይህም ሁሉ የሆነው የፋርስ ንጉሠ ነገሥት ቂሮስ በሰጣቸው ፈቃድ መሠረት ነበር።
እናንተ ከእስራኤል ማኅበረሰብ ግንኙነት የሌላችሁ፥ ለተስፋው ቃል ኪዳን እንግዶች የሆናችሁ፥ በዚህ ዓለምም አንዳች ተስፋ የሌላችሁ፥ ያለ እግዚአብሔር የምትኖሩ፥ ከክርስቶስም የተለያችሁ እንደ ነበራችሁ አስታውሱ።