1 ዜና መዋዕል 2:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዛራሕ ትውልድ አንዱ የሆነው የካርሚ ልጅ ዓካን ለእግዚአብሔር ከተለየው ምርኮ በስርቆት ወስዶ በመደበቁ ምክንያት በእስራኤል ሕዝብ ላይ መቅሠፍት አምጥቶ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የከርሚ ወንድ ልጅ አካን፤ እርሱም ዕርም የሆነ ነገር ሰርቆ በእስራኤል ላይ ጥፋት እንዲመጣ ያደረገ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የከርሚም ልጅ እስራኤልን ያስጨነቀ፥ እርሙንም ሰርቆ የበደለ አካን ነበረ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የዘምሪም ልጅ ከርሚ ነው፤ የከርሚም ልጅ እስራኤልን ያስጨነቀ፥ እርሙን ሰርቆ የበደለ አካን ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የከርሚም ልጅ እስራኤልን ያስጨነቀ፥ እርሙንም ሰርቆ የበደለ አካን ነበረ። |
እግዚአብሔር ከአስፈሪ ቊጣው ተመልሶ ምሕረት ያደርግልህ ዘንድ እንዲወድም ከተወሰነው ሀብት አንዳችም ለራስህ አታስቀር፤ ይህን ብታደርግ ለአባቶችህ በመሐላ በገባው ቃል ኪዳን መሠረት ቊጥርህን ያበዛዋል።
እነዚህንም የረከሱ ጣዖቶች ወደ ቤትህ አታስገባ፤ ብታስገባ ግን አንተም እንደ እነርሱ ትጠፋለህ፤ እነርሱ ለጥፋት የተገቡ ስለ ሆነ በጣም ልትጠላቸውና ልትጸየፋቸው ይገባል።
የዛራ ልጅ ዓካን መደምሰስ በሚገባቸው ነገሮች እምነተቢስ ሆኖ ትእዛዝ በማፍረሱ የእግዚአብሔር ቊጣ በእስራኤል ሕዝብ ሁሉ ላይ አልወረደምን? በጥፋቱም የጠፋው እርሱ ብቻ አልነበረም።’ ”
ኢያሱም “ይህን ሁሉ መከራ በእኛ ላይ ያመጣህብን ስለምንድን ነው? እነሆ! በአንተም ላይ ዛሬ እግዚአብሔር መከራን ያመጣብሃል!” አለው። ከዚህ በኋላ ሕዝቡ ሁሉ ዓካንን በድንጋይ ወግረው ገደሉት፤ ቤተሰቡንም በድንጋይ ወግረው ንብረቱን ሁሉ አቃጠሉ፤