1 ዜና መዋዕል 2:53 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲሁም የቂርያትይዓሪም ቤተሰቦች ዩትራውያን፥ ፑታውያን፥ ሹማታውያንና ሚሽራዓውያን ተብለው የሚጠሩ ነበሩ፤ ከእነርሱም የጾርዓና የኤሽታኦል ትውልድ ተገኙ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲሁም የቂርያትይዓይሪም ጐሣዎች፤ ይትራውያን፣ ፉታውያን፣ ሹማታውያን፣ ሚሽራውያን፣ ጾርዓውያንና ኤሽታኦላውያን ከእነዚህ የመጡ ጐሣዎች ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የቂርያት-ይዓሪምም ወገኖች፤ ይትራውያን፥ ፉታውያን፥ ሹማታውያን፥ ሚሽራውያን ነበሩ፤ ከእነዚህም ጾርዓውያንና ኤሽታኦላውያን ወጡ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የቀርያታርም ወገኖች፤ ይትራውያን፥ ፋታውያን፥ ሹማታውያን፥ ሚሸራውያን፤ ከእነዚህም ሶራሐውያንና ኤሽታአላውያን ወጡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የቂርያትይዓሪምም ወገኖች፤ ይትራውያን፥ ፉታውያን፥ ሹማታውያን፥ ሚሽራውያን፤ ከእነዚህም ጾርዓውያንና ኤሽታኦላውያን ወጡ። |
ስለዚህም የእስራኤል ሕዝብ ጒዞ ጀምረው ከሦስት ቀን በኋላ እነዚህ ሕዝብ ወደሚኖሩባቸው ከተሞች ደረሱ፤ ከተሞቻቸውም ገባዖን፥ ከፊራ፥ በኤሮትና ቂርያትይዓሪም ተብለው ይጠሩ ነበር፤
በዚያን ዘመን ጾርዓ በምትባል ከተማ የሚኖር ማኑሄ የሚባል አንድ ሰው ነበር፤ እርሱም ትውልዱ ከዳን ነገድ ነበር፤ ሚስቱ መኻን ስለ ነበረች ልጆች አልወለደችም፤
ወንድሞቹና የቀሩት ቤተሰቡ ሁሉ መጥተው አስከሬኑን ወሰዱት፤ ወስደውም በጾርዓና በኤሽታኦል መካከል በሚገኘው በአባቱ በማኑሄ መቃብር ቀበሩት፤ ሶምሶን ኻያ ዓመት ሙሉ እስራኤልን መራ።