1 ዜና መዋዕል 18:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሐማት ንጉሥ ቶዒ ዳዊት የጾባን ንጉሥ የሀዳድዔዜርን መላ ሠራዊት ድል እንዳደረገ ሰምቶ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሐማት ንጉሥ ቶዑ፣ ዳዊት የሱባን ንጉሥ የአድርአዛርን ሰራዊት ሁሉ ድል እንደ መታ ሲሰማ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሐማትም ንጉሥ ቶዑ ዳዊት የሱባን ንጉሥ የአድርአዛርን ሠራዊት ሁሉ ድል እንዳደረገ ሰማ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የኤማትም ንጉሥ ቶዑ ዳዊት የሱባን ንጉሥ አድርአዛርን፥ ጭፍራውንም ሁሉ እንደ መታ ሰማ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሐማትም ንጉሥ ቶዑ ዳዊት የሱባን ንጉሥ የአድርአዛርን ጭፍራ ሁሉ እንደ መታ ሰማ። |
ቶዒ ከሀዳድዔዜር ጋር ብዙ ጊዜ ጦርነት አድርጎ ስለ ነበር፥ ንጉሥ ዳዊትን እጅ እንዲነሣና በሀዳድዔዜር ላይ ስለ ተቀዳጀው ድል ደስታውን እንዲገልጥለት ልጁን ዮራምን ወደ ዳዊት ላከ። ዮራምም ከወርቅ፥ ከብርና ከነሐስ የተሠሩ ዕቃዎችን ገጸ በረከት አድርጎ ለዳዊት አመጣለት፤
እንዲሁም የሀዳድዔዜር ግዛት ከነበሩት ከጢብሐትና ከኩን ከተማዎች እጅግ ብዙ የሆነ ነሐስ ወሰደ፤ ዘግየት ብሎም ሰሎሞን በነሐሱ የቤተ መቅደሱን ገንዳ፥ ዐምዶችና የነሐስ ዕቃዎች አሠራበት።
ዐሞናውያን በገዛ እጃቸው ዳዊትን ጠላት እንዳደረጉት ተገነዘቡ፤ ስለዚህም ሠላሳ አራት ሺህ ኪሎ የሚመዝን ብር ከፍለው ሠረገሎችንና ፈረሰኞችን ከላይኛው መስጴጦምያና የሶርያ ግዛቶች ከሆኑት ከማዕካና ከጾባ ተከራዩ፤