1 ዜና መዋዕል 17:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “አሁንም እግዚአብሔር አምላክ ሆይ፥ ስለ እኔና ስለ ዘሮቼ የተናገርከውን የተስፋ ቃል ሁሉ ፈጽም፤ አደርጋለሁ ያልከውንም ሁሉ አድርግ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እግዚአብሔር ሆይ፤ አሁንም ለባሪያህና ለቤቱ የሰጠኸውን ተስፋ ለዘላለም የጸና ይሁን፤ እንደተናገርኸውም ፈጽም፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሁንም፥ አቤቱ፥ ስለ ባርያህና ስለ ቤቱ የተናገርኸው ቃል ለዘለዓለም የጸና ይሁን፤ እንደ ተናገርህም አድርግ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሁንም፥ አቤቱ፥ ስለ ባሪያህና ስለ ቤቱ የተናገርኸው ቃል ለዘለዓለም የታመነ ይሁን፤ እንደ ተናገርህም አድርግ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሁንም፥ አቤቱ! ስለ ባሪያህና ስለ ቤቱ የተናገርኸው ለዘላለም የጸና ይሁን፤ እንደ ተናገርህም አድርግ። |
ይህንንም የምታደርገው ስምህ ለዘለዓለም የገነነ ይሆን ዘንድና ሰዎችም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር የእስራኤል አምላክ ነው እንዲሉ ነው፤ የእኔ የአገልጋይህ ቤትም በፊትህ የጸና ይሆናል።
የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር፥ ይሁዳን በእስራኤል ላይ መሪ ነገድ አድርጎ መርጦታል፤ ከይሁዳም የእኔን ቤተሰብ፥ ከእኔም ቤተሰብ እኔን የእስራኤል ንጉሥ እንድሆን መረጠኝ፤ የእኔም ዘሮች ነገሥታት ሆነው እንደሚያስተዳድሩ ቃል ገብቶልኛል።
እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ! ለአባቴ የሰጠኸው የተስፋ ቃል እንዲፈጸም አድርግ፤ እነሆ ከብዛቱ የተነሣ ሊቈጠር በማይችል ሕዝብ ላይ አንግሠኸኛል፤
ይህም ከሆነ አሁን ያሉባትን በማርና በወተት የበለጸገችውን ለምለም ምድር የቀድሞ አባቶቻቸው እንዲወርሱ ባደረግሁ ጊዜ የሰጠኋቸውን የተስፋ ቃል እፈጽማለሁ።” እኔም “እሺ ጌታ ሆይ!” አልኩ።