ይሁን እንጂ ንጉሡ፥ አቤሴሎም በቤተ መንግሥት ውስጥ እንዳይኖር ትእዛዝ ሰጠ፤ ደግሞም ንጉሡ “ከቶ እርሱን ማየት አልፈልግም” አለ። ስለዚህ አቤሴሎም በራሱ ቤት ኖረ፤ ወደ ንጉሡም ፊት ቀርቦ አልታየም።
1 ዜና መዋዕል 15:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዳዊት የሚኖርባቸውን ቤቶች በራሱ ከተማ በኢየሩሳሌም ሠራ፤ የእግዚአብሔር የቃል ኪዳን ታቦት የሚኖርበትንም ስፍራ አዘጋጅቶ ድንኳን ተከለለት፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዳዊት በስሙ በተጠራችው ከተማ ለራሱ ቤቶችን ሠራ፤ ለእግዚአብሔር ታቦት ቦታ አዘጋጅቶ ድንኳን ተከለ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዳዊትም በራሱ ከተማ ላይ ለራሱ ቤቶችን ሠራ፤ ለእግዚአብሔርም ታቦት ስፍራ አዘጋጀ፥ ድንኳንም ተከለለት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊትም በከተማው ለራሱ ቤቶችን ሠራ፤ ለእግዚአብሔርም ታቦት ስፍራ አዘጋጀ፤ ድንኳንም ተከለላት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳዊትም በከተማው ላይ ለራሱ ቤቶችን ሠራ፤ ለእግዚአብሔርም ታቦት ስፍራ አዘጋጀ፤ ድንኳንም ተከለለት። |
ይሁን እንጂ ንጉሡ፥ አቤሴሎም በቤተ መንግሥት ውስጥ እንዳይኖር ትእዛዝ ሰጠ፤ ደግሞም ንጉሡ “ከቶ እርሱን ማየት አልፈልግም” አለ። ስለዚህ አቤሴሎም በራሱ ቤት ኖረ፤ ወደ ንጉሡም ፊት ቀርቦ አልታየም።
ዳዊት ምሽጉን ከያዘ በኋላ መኖሪያውን በዚያው ስፍራ አደረገ፤ እርስዋንም “የዳዊት ከተማ” ብሎ ጠራት፤ ከኮረብታው በስተ ምሥራቅ በኩል በዐፈር ከተደለደለው ስፍራ አንሥቶ በኮረብታው ዙሪያ ከተማይቱንም ሠራ።
በቃል ኪዳኑ ታቦት ምክንያት እግዚአብሔር የዖቤድኤዶምን ቤተሰብና ያለውን ነገር ሁሉ እግዚአብሔር የባረከለት መሆኑን ንጉሥ ዳዊት ሰማ፤ ስለዚህም የቃል ኪዳኑን ታቦት በታላቅ ደስታ ወደ ኢየሩሳሌም ሊወስደው በማሰብ ወደ ዖቤድኤዶም ቤት ሄዶ አወጣው።
ታቦቱንም አምጥተው ዳዊት ባዘጋጀለት ድንኳን ውስጥ በተመደበለት ስፍራ አኖሩት፤ ከዚህም በኋላ ዳዊት የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የአንድነት መሥዋዕት ሁሉ ለእግዚአብሔር አቀረበ።
ሌዋውያኑንም እንዲህ አላቸው፤ “እነሆ እናንተ ለሌዋውያን ጐሣዎች መሪዎች ናችሁ፤ የእስራኤል አምላክን የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ታቦት እኔ ወዳዘጋጀሁለት ስፍራ ተሸክማችሁ ታመጡ ዘንድ ራሳችሁንና ሌዋውያን ወገኖቻችሁን ሁሉ ቀድሱ፤
የቃል ኪዳኑንም ታቦት ወስደው ዳዊት ባዘጋጀው ድንኳን ውስጥ አኖሩት፤ ከዚያም በኋላ በሙሉ የሚቃጠል መሥዋዕትንና የኅብረት መሥዋዕትን ለእግዚአብሔር አቀረቡ፤
ከዚህ በኋላ ንጉሥ ሰሎሞን የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ታቦት የዳዊት ከተማ ከሆነችው ከጽዮን ወደ ቤተ መቅደሱ ያመጡ ዘንድ የእስራኤል ሽማግሌዎች፥ የነገድና የቤተሰብ አለቆች ሁሉ በኢየሩሳሌም እንዲሰበሰቡ ትእዛዝ ሰጠ።