1 ዜና መዋዕል 11:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዳዊትም ሄዶ በምሽጉ ውስጥ ስለ ኖረ ያቺ ስፍራ “የዳዊት ከተማ” ተብላ ተጠራች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ዳዊት መኖሪያውን በዐምባዪቱ ውስጥ አደረገ፤ ከዚህም የተነሣ የዳዊት ከተማ ተባለች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዳዊትም በአምባይቱ ውስጥ ተቀመጠ፤ ስለዚህም የዳዊት ከተማ ብለው ጠሩአት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊትም በአንባዪቱ ውስጥ ተቀመጠ፤ ስለዚህም “የዳዊት ከተማ” ብለው ጠሩአት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳዊትም በአምባይቱ ውስጥ ተቀመጠ፤ ስለዚህም “የዳዊት ከተማ” ብለው ጠሩአት። |
ኢያቡሳውያን ዳዊትን “ከቶ ወደዚህ አትገባም” አሉት፤ ዳዊት ግን በጽዮን የሠሩትን ምሽጋቸውን ያዘ፤ ከዚያም በኋላ ያቺ ስፍራ “የዳዊት ከተማ” ተብላ ትጠራ ጀመር።
ዳዊትም “በመጀመሪያ በኢያቡሳውያን ላይ አደጋ የሚጥል ሰው የሠራዊቱ አዛዥ ይሆናል!” አለ፤ የጸሩያ ልጅ ኢዮአብ በመጀመሪያ ሄዶ በኢያቡሳውያን ላይ አደጋ በመጣሉ የሠራዊቱ አዛዥ ሆነ፤
ዳዊት ከኰረብታው በስተ ምሥራቅ በኩል በዐፈር ከተደለደለው ስፍራ አንሥቶ ከተማይቱን እንደገና ሠራ፤ ኢዮአብም በበኩሉ የቀረውን የከተማይቱን ክፍል ሠራ፤