1 ዜና መዋዕል 1:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ያፌትም ጎሜር፥ ማጎግ፥ ማዳይ፥ ያዋን፥ ቱባል፥ ሜሼክና ቲራስ ተብለው የሚጠሩ ወንዶች ልጆችን ወለደ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የያፌት ልጆች፦ ጎሜር፣ ማጎግ፣ ማዴ፣ ያዋን፣ ቶቤል፣ ሜሼኽ፣ ቴራስ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የያፌት ልጆች፤ ጋሜር፥ ማጎግ፥ ማዴ፥ ያዋን፥ ቶቤል፥ ሞሳሕ፥ ቴራስ ናቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የያፌት ልጆች ጋሜር፥ ማጎግ፥ ማዳይ፥ ይሕያን፥ ኤልሳ፥ ቶቤል፥ ሞሳሕና ቲራም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የያፌት ልጆች፤ ጋሜር፥ ማጎግ፥ ማዴ፥ ያዋን፥ ቶቤል፥ ሞሳሕ፥ ቴራስ። |
ከግሪኮች ከቱባልና ከሜሼክ ጋር የንግድ ሥራ ታካሂጂ ነበር፤ ባሪያዎችንና ከነሐስ የተሠሩ ዕቃዎችን ወስደሽ፥ በምትኩ ሸቀጥሽን ትሰጪአቸው ነበር፤
ጎሜር ከሠራዊቱ ሁሉ ጋርና፥ ራቅ ካለው የሰሜን ክፍልም ቤት ቶጋርማና ሠራዊቱ ከእርሱ ጋር ናቸው፤ እንዲሁም ከሌሎች ብዙዎች አገሮች የመጡ ሰዎች ከእርሱ ጐን ተሰልፈዋል።
ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ አለ፦ “የሰው ልጅ ሆይ! የሜሼክና የቱባል ሕዝብ ገዢ በሆነው በጎግ ላይ ትንቢት ተናገርበት፤ በእርሱም ላይ የተነሣሁ መሆኔን ንገረው።