1 ዜና መዋዕል 1:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኦፊርን፥ ሐዊላና ዮባብን ወለደ። እነዚህ ሁሉ የዮቅጣን ልጆች ነበሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኦፊርን፣ ኤውላጥን፣ ዮባብን ወለደ፤ እነዚህ ሁሉ የዮቅጣን ወንዶች ልጆች ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኦፊርን፥ ሐዊላን፥ ዮባብን ነበር፤ እነዚህ ሁሉ የዮቅጣን ልጆች ነበሩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኦፌርን፥ ሄውላን፥ ኦራምን፥ ዑካብን ወለደ፤ እነዚህ ሁሉ የዮቅጣን ልጆች ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኦፊርን፥ ኤውላጥን፥ እና ዮባብን ወለደ፤ እነዚህ ሁሉ የዮቅጣን ልጆች ነበሩ። |
የእስማኤል ዘሮች ከግብጽ በስተምሥራቅ ወደ አሦር በምትወስደው መንገድ በሐዊላና በሹር መካከል ይኖሩ ነበር፤ የኖሩትም ከሌሎቹ የአብርሃም ዘሮች ጋር በጥላቻ ተራርቀው ነበር።
እነርሱም በመርከብ ተጒዘው ወደ ኦፊር ምድር ከሄዱ በኋላ ወደ ንጉሡ ወደ ሰሎሞን ሲመለሱ ከዐሥራ አራት ሺህ ኪሎ ግራም በላይ የሚመዝን ወርቅ ይዘውለት መጡ።
በቤተ መንግሥትህ ከሚገኙት ወይዛዝርት መካከል፥ የነገሥታት ሴቶች ልጆች ይገኛሉ፤ ንግሥቲቱም በንጹሕ ወርቅ ያሸበረቀ ጌጠኛ ልብስ ተጐናጽፋ ከዙፋንህ በስተቀኝ ቆማለች።