ሰሎሞን ከሊባኖስ ዛፍ ጀምሮ በቤት ግንብ ላይ እስከሚበቅለው ሂሶጵ ድረስ ስለ ዛፎችና ስለ ተክሎች በምሳሌ እየመሰለ ተናግሮአል፤ እንዲሁም ስለ ልዩ ልዩ እንስሶች፥ ስለ ወፎች በሆዳቸው እየተሳቡ ስለሚሄዱ ፍጥረቶችና ስለ ዓሣዎችም አስተምሮአል።
ማሕልየ መሓልይ 5:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እግሮቹ በምዝምዝ ወርቅ ላይ የተመሠረቱ የዕብነ በረድ ምሰሶች ናቸው፥ መልኩ እንደ ሊባኖስ፥ እንደ ዝግባ ዛፍ ምርጥ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግሮቹ በንጹሕ ወርቅ መቆሚያ ላይ የተተከሉ፣ የዕብነ በረድ ምሰሶዎችን ይመስላሉ፤ መልኩ እንደ ሊባኖስ ነው፤ እንደ ዝግባ ዛፎቹም ምርጥ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግሮቹ በወርቅ መሠረት ላይ የተተከሉ የዕብነበረድ ምሰሶዎችን ይመስላሉ፤ መልኩ በሊባኖስ ዛፍ እንዳጌጠ እንደ ሊባኖስ ተራራ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግሮቹ በምዝምዝ ወርቅ እንደ ተመሠረቱ እንደ ዕብነ በረድ ምሰሶዎች ናቸው፤ መልኩ እንደ ሊባኖስና እንደ ዝግባ ዛፍ የተመረጠ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግሮቹ በምዝምዝ ወርቅ እንደ ተመሠረቱ እንደ ዕብነ በረድ ምሰሶች ናቸው፥ መልኩ እንደ ሊባኖስና እንደ ዝግባ ዛፍ መልካም ነው። |
ሰሎሞን ከሊባኖስ ዛፍ ጀምሮ በቤት ግንብ ላይ እስከሚበቅለው ሂሶጵ ድረስ ስለ ዛፎችና ስለ ተክሎች በምሳሌ እየመሰለ ተናግሮአል፤ እንዲሁም ስለ ልዩ ልዩ እንስሶች፥ ስለ ወፎች በሆዳቸው እየተሳቡ ስለሚሄዱ ፍጥረቶችና ስለ ዓሣዎችም አስተምሮአል።
አንገትሽ እንደ ዝሆን ጥርስ ግንብ ነው፥ ዐይኖችሽ በሐሴቦን ውስጥ በባትረቢ በር አጠገብ የሚግኙ ኩሬዎች ናቸው፥ አፍንጫሽ ወደ ደማስቆ እንደሚመለከት እንደ ሊባኖስ ግንብ ነው።
ከፍ ባለው በእስራኤል ተራራ ላይ እተክለዋለሁ፥ ቅርንጫፎችም ያወጣል፥ ፍሬም ያፈራል፥ የተዋበ ዝግባ ይሆናል፥ በበታቹም ወፎች ሁሉ ይኖራሉ፥ በቅርንጫፎቹም ጥላ በክንፍ የሚበርሩ ሁሉ ይቀመጣሉ።
በእግዚአብሔር ገነት የነበሩ ዝግባዎች አልሸፈኑትም፥ ጥዶችም ቅርጫፎቹን አይመስሉትም አስታ የሚባለውም ዛፍ ቅርጫፎቹን አይመሳሰሉትም ነበር፤ በእግዚአብሔር ገነት የነበረ ዛፍ ሁሉ በውበቱ አይመስለውም ነበር።
የሃይማኖታችን ምሥጢር ያለ ጥርጥር ታላቅ ነው፤ እርሱም፦ በሥጋ ተገለጠ፥ በመንፈስ ጸደቀ፥ ለመላእክት ታየ፥ በአሕዛብ መካከል ተሰበከ፥ በመላው ዓለም ታመነ፥ በክብር ዐረገ፥ የሚል ነው።
ከዚያም ሴቲቱ ወደ ባሏ ሄዳ እንዲህ አለችው፤ “የእግዚአብሔር ሰው ወደ እኔ መጣ፤ የእግዚአብሔር መልአክ የሚመስልና እጅግ የሚያስደነግጥ ነበር። ከየት እንደመጣ አልጠየቅሁትም፤ እርሱም ስሙን አልነገረኝም፤