ዮዲት በሆሎፎርኒስና በጦር አለቆቹ ፊት በመጣች ጊዜ፥ በቁንጅናዋ ሁሉም ተደነቁ፤ እርሷም በግንባርዋ ተደፍታ እጅ ነሣችለት፥ አሽከሮቹ ግን አነሷት።
ዮዲትም ወደ እርሱ በቀረበች ጊዜ አሽከሮቹ ቆመው ነበር፤ ከመልኳ ደም ግባት የተነሣ ሁሉም ተደነቁ፤ እርሷም በግንባሯ በምድር ላይ ወድቃ ሰገደችለት፤ አሽከሮቹም አነሡአት።