ሕዝቅኤል 46:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን ከባርያዎቹ ለአንዱ ከርስቱ ስጦታ ቢሰጥ እስከ ነጻነት ዓመት ድረሰ ለእርሱ ይሁን፥ ከዚያም በኋላ ለመስፍኑ ይመለስለት፤ ርስቱ ለልጆቹ ብቻ ይሁን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይሁን እንጂ ገዥው ከርስቱ ላይ ከባሪያዎቹ ለአንዱ ቢሰጥ፣ ባሪያው ነጻ እስከሚወጣበት ዓመት ድረስ የራሱ ሊያደርገው ይችላል፤ ከዚያም ርስቱ ለገዢው ይመለስለታል፤ ርስቱም ለወንድ ልጆቹ ብቻ የሚተላለፍ ይሆናል፤ የእነርሱም ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን በሥልጣን ላይ ያለው መስፍኑ የራሱ ድርሻ ከሆነው ርስት ከፍሎ ከአገልጋዮቹ ለአንዱ ቢሰጥ፥ በኀምሳ ዓመት ዞሮ በሚመጣው በኢዮቤልዩ ዓመት ለመስፍኑ ይመለስለት፤ ንብረቱ የራሱ ስለ ሆነ ይዞታው ለዘለዓለሙ የእርሱና የልጆቹ ብቻ መሆን አለበት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን ከአገልጋዮቹ ለአንዱ ከርስቱ ስጦታ ቢሰጥ እስከ ነፃነት ዓመት ድረስ ለእርሱ ይሁን፥ ከዚያም በኋላ ለአለቃው ይመለስ፤ ርስቱ ግን ለልጆቹ ይሁን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን ከባሪያዎቹ ለአንዱ ከርስቱ ስጦታ ቢሰጥ እስከ ነጻነት ዓመት ድረሰ ለእርሱ ይሁን፥ ከዚያም በኋላ ለአለቃው ይመለስ፥ ርስቱ ግን ለልጆቹ ይሁን። |
ኀምሳኛውንም ዓመት ትቀድሳላችሁ፥ በምድሪቱም ለሚኖሩባት ሁሉ ነጻነትን ታውጃላችሁ፤ እርሱ ለእንናተ ኢዮቤልዩ ይሆናል፤ ከእናንተም እያንዳንዱ ሰው ወደ ርስቱና ወደ ወገኑ ይመለሳል።