እኔም እንዲህ አልሁ፦ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፥ ወይኔ! እነሆ፥ ሰውነቴ አልረከሰችም፥ ከልጅነቴ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ፥ የሞተ ወይም እንስሳ የገደለውን ከቶ አልበላሁም፥ ርኩስም ሥጋ በአፌ ውስጥ አልገባም።
ሕዝቅኤል 44:31 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ካህናቱ የሞተ ወይም ሌላ አውሬ የገደለውን ወፍ ወይም እንስሳ አይብሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ካህናት ሞቶ የተገኘውን ወይም በዱር አራዊት የተዘነጠለውን ወፍም ይሁን ሌላ እንስሳ፣ ማንኛውንም ነገር መብላት የለባቸውም።’ ” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ካህናቱ ሞቶ የተገኘውን ወይም ሌላ አውሬ የገደለውን የወፍ ወይም የእንስሳ ሥጋ አይብሉ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዎፍም ሆነ ከእንስሳ የበከተውንና አውሬ የሰበረውን ካህናት አይብሉት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የበከተውንና የተሰበረውን፥ ወፍ ወይም እንስሳ ቢሆን፥ ካህናት አይብሉት። |
እኔም እንዲህ አልሁ፦ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፥ ወይኔ! እነሆ፥ ሰውነቴ አልረከሰችም፥ ከልጅነቴ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ፥ የሞተ ወይም እንስሳ የገደለውን ከቶ አልበላሁም፥ ርኩስም ሥጋ በአፌ ውስጥ አልገባም።
ከበድኑም የሚበላ ልብሱን ያጥባል፥ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል፤ እንዲሁም በድኑን የሚያነሣ ልብሱን ያጥባል፥ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል።
የሞተውን ወይም አውሬ የገደለውን የሚበላ ሰው ሁሉ፥ የአገሩ ተወላጅ ወይም እንግዳ ቢሆን፥ ልብሱን ያጥባል፥ በውኃም ይታጠባል፥ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል፤ ከዚያም በኋላ ንጹሕ ይሆናል።
“አንተ ግን ለጌታ ለእግዚአብሔር ቅዱስ ሕዝብ ነህና የሞተውን ሁሉ አትብላ፤ ከከተሞችህ በአንዲቱ ለሚኖር መጻተኛ እንዲበላ ልትሰጠው ትችላለህ፤ ወይም ለውጭ አገር ሰው ልትሸጠው ትችላለህ። የፍየልን ግልገል በእናቱ ወተት አትቀቅል።