እንዲህም አለኝ፦ “ካህናቱ ሕዝቡን ለመቀደስ ወደ ውጭው አደባባይ እንዳያወጡ የበደሉን መሥዋዕትና የኃጢአቱን መሥዋዕት የሚቀቅሉበት፥ የእህሉንም ቁርባን የሚጋግሩበት ስፍራ ይህ ነው።”
ሕዝቅኤል 44:29 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእህሉን ቁርባን፥ የኃጢአትን መሥዋዕትና የበደልን መሥዋዕት ይበላሉ፤ በእስራኤልም እርም የሆነው ነገር ሁሉ ለእነርሱ ይሆናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእህሉን ቍርባን፣ የኀጢአቱንና የበደሉን መሥዋዕት ይበላሉ፤ በእስራኤል ለእግዚአብሔር የተሰጠው ሁሉ የእነርሱ ይሆናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእህሉ መሥዋዕት፥ የኃጢአትና የበደል ስርየት መሥዋዕት ለእነርሱ ምግብ ይሁንላቸው፤ በእስራኤል ምድር ለእኔ ተለይቶ የተቀደሰውን ማናቸውንም መባ ሁሉ ይቀበሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእህሉን ቍርባንና የኀጢአትን መሥዋዕት የንስሓንም መሥዋዕት ይበላሉ፤ በእስራኤልም ዘንድ እርም የሆነው ነገር ሁሉ ለእነርሱ ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእህሉን ቍርባንና የኃጢአትን መሥዋዕት የበደልንም መሥዋዕት ይበላሉ፥ በእስራኤልም ዘንድ እርም የሆነው ነገር ሁሉ ለእነርሱ ይሆናል። |
እንዲህም አለኝ፦ “ካህናቱ ሕዝቡን ለመቀደስ ወደ ውጭው አደባባይ እንዳያወጡ የበደሉን መሥዋዕትና የኃጢአቱን መሥዋዕት የሚቀቅሉበት፥ የእህሉንም ቁርባን የሚጋግሩበት ስፍራ ይህ ነው።”
“ነገር ግን ሰው የእርሱ ከሆነው ነገር ሁሉ ለጌታ ለይቶ እርም ያደረገው፥ ሰው ቢሆን ወይም እንስሳ ወይም የርስቱ እርሻ ቢሆን፥ አይሸጥም፥ አይቤዥም፤ እርም የሆነ ነገር ሁሉ ለጌታ እጅግ የተቀደሰ ነው።