ሕዝቅኤል 44:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዳይረክሱ ወደ ሞተ ሰው አይግቡ፤ ነገር ግን ለአባት ወይም ለእናት ወይም ለወንድ ልጅ ወይም ለሴት ልጅ ወይም ለወንድም ወይም ላላገባች እኅት ይርከሱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘ካህን ወደ ሞተ ሰው ሬሳ በመጠጋት ራሱን አያርክስ፤ ይሁን እንጂ ሟች አባቱ ወይም እናቱ፣ ወንድ ልጁ ወይም ሴት ልጁ፣ ወንድሙ ወይም ያላገባች እኅቱ ብትሆን፣ ራሱን ማርከስ ይችላል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ከወላጆቹ አንዱ፥ ከልጆቹ አንዱ፥ ወይም ወንድሙ ወይም ያላገባች እኅቱ ካልሆኑ በቀር ማንኛውም ካህን የሌላ ሰው ሬሳ በመንካት ራሱን ማርከስ አይገባውም፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዳይረክሱም ወደ ሞተ ሰው አይግቡ፤ ነገር ግን ለአባት፥ ወይም ለእናት፥ ወይም ለወንድ ልጅ፥ ወይም ለሴት ልጅ፥ ወይም ለወንድም፥ ወይም ላልተዳረች እኅት ይርከሱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዳይረክሱም ወደ ሞተ ሰው አይግቡ፥ ነገር ግን ለአባት ወይም ለእናት ወይም ለወንድ ልጅ ወይም ለሴት ልጅ ወይም ለወንድም ወይም ላልተዳረች እኅት ይርከሱ። |
ከአሮን ዘር ማናቸውም ሰው የለምጽ ደዌ ወይም ፈሳሽ ነገር ያለበት፥ ንጹሕ እስኪሆን ድረስ ከተቀደሱት ነገሮች አይብላ። በበድን፥ ወይም ዘሩ በሚፈስስበት ሰው የረከሰውን ነገር የሚነካ፥
ስለዚህ ከአሁን ጀምሮ ማንንም በሰብአዊ አመለካከት እንደምናየው አድርገን አንመለክትም፤ ክርስቶስንም በዚህ መልክ ተመልክተነው የነበርን ብንሆን እንኳን፥ ከእንግዲህ ወዲህ ግን በዚህ መልክ አይደለም የምናውቀው።