ሰሎሞንም ኻያ ሁለት ሺህ የቀንድ ከብቶችንና አንድ መቶ ኻያ ሺህ በጎችን የኅብረት መሥዋዕት አድርጎ አቀረበ፤ በዚህም ዓይነት ንጉሥ ሰሎሞንና እስራኤላውያን ሁሉ ቤተ መቅደሱ ለእግዚአብሔር የተለየ እንዲሆን አደረጉ።
ሕዝቅኤል 36:38 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንደ ተቀደሰ መንጋ፥ በበዓላቶችዋ ቀን እንደሚሆኑ እንደ ኢየሩሳሌም መንጋ፥ እንዲሁም የፈረሱት ከተሞች በሰዎች መንጋ ይሞላሉ፤ እኔም ጌታ እንደሆንሁ ያውቃሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በኢየሩሳሌም በዓላት ላይ እንደሚገኘው የመሥዋዕት በግ መንጋ አበዛዋለሁ። እነሆ! ፈራርሰው የነበሩት ከተሞች የብዙ ሕዝብ መኖሪያ ይሆናሉ፤ ከዚያም እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።’ ” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቀድሞ ኢየሩሳሌም በበዓል ቀን ለመሥዋዕት በሚቀርቡ በጎች ትሞላ እንደ ነበረች የፈራረሱት ከተሞች በሕዝብ የተሞሉ ይሆናሉ፤ በዚያን ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንኩ ያውቃሉ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንደ ተቀደሱ በጎች፥ በበዓላቶችዋ ቀን እንደሚሆኑ እንደ ኢየሩሳሌም በጎች እንዲሁ የፈረሱት ከተሞች በሰዎች መንጋ ይሞላሉ፤ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንደ ተቀደሱ በጎች፥ በበዓላቶችዋ ቀን እንደሚሆኑ እንደ ኢየሩሳሌም በጎች፥ እንዲሁ የፈረሱት ከተሞች በሰዎች መንጋ ይሞላሉ፥ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ። |
ሰሎሞንም ኻያ ሁለት ሺህ የቀንድ ከብቶችንና አንድ መቶ ኻያ ሺህ በጎችን የኅብረት መሥዋዕት አድርጎ አቀረበ፤ በዚህም ዓይነት ንጉሥ ሰሎሞንና እስራኤላውያን ሁሉ ቤተ መቅደሱ ለእግዚአብሔር የተለየ እንዲሆን አደረጉ።
ሰሎሞንም ከእርሱም ጋር እጅግ ታላቅ ጉባኤ የሆኑ፥ ከሐማት መግቢያ ጀምሮ እስከ ግብጽ ወንዝ ድረስ ያሉ እስራኤል ሁሉ፥ በዚያን ጊዜ ሰባት ቀን በዓል አደረጉ።
ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ አሁንም የእስራኤል ቤት እንድሠራላቸው እንዲፈልጉኝ እፈቅድላቸዋለሁ፥ ሰዎችንም እንደ መንጋ አበዛላቸዋለሁ።
የምድሪቱ ሕዝብ ግን በየክብረ በዓሉ ቀን ወደ ጌታ ፊት በመጡ ጊዜ በሰሜን በር በኩል ሊሰግድ የገባው በደቡብ በር በኩል ይውጣ፥ በደቡብ በር የገባው በሰሜን በር በኩል ይውጣ፤ በፊት ለፊት ባለው ይውጣ እንጂ በገባበት በር አይመለስ።
“በዓመት ሦስት ጊዜ ወንዶች ሁሉ በቂጣ በዓል፥ በመከርንና በዳስ በዓል፥ በአምላክህ በጌታ ፊት እርሱ በመረጠው ስፍራ ይታዩ፥ በጌታም ፊት ባዶ እጃቸውን አይታዩ።