ሕዝቅኤል 35:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ እኔ ሕያው ነኝና ይላል ጌታ እግዚአብሔር፥ እነርሱን ጠልተህ እንዳደረግኸው እንደ ቁጣህና እንደ ቅናትህ መጠን አደርጋለሁ፤ በፈረድሁብህም ጊዜ በእነርሱ መካከል ማንነቴን አስታውቃለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ በሕያውነቴ እምላለሁ፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ ከጥላቻችሁ የተነሣ በእነርሱ ላይ በገለጣችሁት ቍጣና ቅናት ልክ እፈርድባችኋለሁ፤ በእናንተም ላይ በምፈርድበት ጊዜ፣ ማንነቴ በእነርሱ መካከል እንዲታወቅ አደርጋለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህም እኔ ልዑል እግዚአብሔር ሕያው እንደ መሆኔ በሕዝቤ ላይ ባላችሁ ጥላቻ ምክንያት ያሳያችሁት ቊጣና ምቀኝነት ሁሉ ተገቢውን ቅጣት እሰጣችኋለሁ። እነርሱም እናንተን በምቀጣበት ጊዜ የምቀጣችሁ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን እንዲያውቁ አደርጋለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህ እኔ ሕያው ነኝ! እንደ ቍጣህ መጠን፥ እነርሱንም ጠልተህ እንዳደረግኸው እንደ ቅንአትህ መጠን እኔ እፈርድብሃለሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ በፈረድሁብህም ጊዜ በእነርሱ ዘንድ የታወቅሁ እሆናለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህ እኔ ሕያው ነኝና እንደ ቍጣህ መጠን እነርሱንም ጠልተህ እንዳደረግኸው እንደ ቅንዓትህ መጠን እኔ እሠራለሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፥ በፈረድሁብህም ጊዜ በእነርሱ ዘንድ የታወቅሁ እሆናለሁ። |
በሕዝቤ በእስራኤል እጅ ኤዶምን እበቀላለሁ፤ እንደ ቁጣዬና እንደ መዓቴ መጠን በኤዶም ላይ ያደርጋሉ፤ በቀሌንም ያውቃሉ፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
ጌታ እንዲህ ይላል፦ “ወንድሙን በሰይፍ አሳድዶታልና፥ ርኅራኄውንም ሁሉ አጥፍቷልና፥ ባለማቋረጥም ተቆጥቷልና፥ መዓቱንም ለዘለዓለም ጠብቆአልና ስለ ሦስት የኤዶምያስ ኃጢአት ስለ አራትም መቅሠፍቴን ከማድረግ አልመለስም።