ሕዝቅኤል 34:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔ ራሴ በጎቼን አሰማራለሁ አስመስጋቸዋለሁም፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኔ ራሴ በጎቼን አሰማራለሁ፤ አስመስጋቸዋለሁም። ይላል ጌታ እግዚአብሔር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔ ራሴ ለበጎቼ እረኛ እሆናለሁ፤ እንዲያርፉም አደርጋቸዋለሁ፤ እኔ ልዑል እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።’ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔ ራሴ በጎችን አሰማራለሁ፤ አስመስጋቸውማለሁ፤ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔ ራሴ በጎቼን አሰማራለሁ አስመስጋቸውማለሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር። |
የተመሸገችው ከተማ ብቻዋን ሆነች፤ እንደ ምድረ በዳ ሆና የተተወች መኖሪያ ሆናለች፤ በዚያም ጥጃ ይሰማራል፥ በዚያም ይተኛል ቅርንጫፍዋንም ይበላል።
ሕዝቤ የጠፉ በጎች ሆነዋል፤ እረኞቻቸው አሳቱአቸው፥ ከተራሮችም ላይ እንዲያፈገፍጉ አደረጉአቸው፤ ከተራራ ወደ ኮረብታ ሄደዋል፥ በረታቸውንም ረስተዋል።
የሰው ልጅ ሆይ፥ ትንቢት ተናገር፥ በእስራኤል እረኞች ላይ ትንቢት ተናገር፥ እረኞቹንም እንዲህ በላቸው፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ራሳቸውን ለመገቡ ለእስራኤል እረኞች ወዮላቸው! እረኞች በጎችን ማሰማራት አይገባቸውምን?
የእስራኤል ትሩፍ ኃጢአትን አይሠሩም፥ ሐሰትንም አይናገሩም፥ በአፋቸውም ውስጥ አታላይ ምላስ አይገኝም፤ እነርሱም ይሰማራሉ፥ ይተኛሉ፥ የሚያስፈራቸውም የለም።
ከበሉ በኋላም ኢየሱስ ስምዖን ጴጥሮስን “የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ! ከእነዚህ ይበልጥ ትወደኛለህን?” አለው። “አዎን ጌታ ሆይ! እንደምወድህ አንተ ታውቃለህ፤” አለው። ኢየሱስም “ግልገሎቼን አሰማራ፤” አለው።