La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ሕዝቅኤል 31:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ወደ ሲኦል በወረደበት ቀን ልቅሶ አስለቀስሁ፥ ቀላዩን ስለ እርሱ ሸፈንሁት፥ ፈሳሾቹን ገታሁ፥ ታላላቆችም ውኆች ተከለከሉ፤ ሊባኖስንም ስለ እርሱ አሳዘንሁት፥ የዱርም ዛፎች ሁሉ ስለ እርሱ ዛሉ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

“ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ወደ መቃብር በወረደበት ቀን ጥልቅ ምንጮችን ስለ እርሱ በሐዘን ሸፈንኋቸው፤ ወንዞቹን ገታሁ፤ ታላላቅ ፈሳሾችም ተቋረጡ። በርሱም ምክንያት ሊባኖስን ጨለማ አለበስሁ፤ የደን ዛፎችም ሁሉ ደረቁ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ልዑል እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው፦ “ያ ዛፍ ተቈርጦ ወደ ሙታን ዓለም በሚወርድበት ጊዜ ጥልቁን ውሃ ዘግቼ እየተለቀሰለት ይሸፈናል። ወንዞችም እንዲቋረጡ አደርጋለሁ፤ ኀይለኞቹ ወራጅ ውሃዎችም እንዲቆሙ ይደረጋሉ። በዚህም ምክንያት በሊባኖስ ተራራዎች ላይ የጨለማ ግርዶሽ አመጣለሁ፤ ስለዚህም የሜዳ ዛፎች ሁሉ ይጠወልጋሉ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

“ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ወደ ሲኦል በወ​ረ​ደ​በት ቀን ልቅ​ሶን አስ​ለ​ቀ​ስሁ፤ ቀላ​ዩ​ንም ስለ እርሱ ሸፈ​ን​ሁት፤ ፈሳ​ሾ​ች​ንም ከለ​ከ​ልሁ፤ ታላ​ላ​ቆ​ችም ውኆች ተከ​ለ​ከሉ፤ ሊባ​ኖ​ስ​ንም ስለ እርሱ አሳ​ዘ​ን​ሁት። የዱ​ርም ዛፎች ሁሉ ስለ እርሱ ዛሉ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ወደ ሲኦል በወረደበት ቀን ልቅሶ አስለቀስሁ፥ ቀላዩንም ስለ እርሱ ሸፈንሁት ፈሳሾቹንም ከለከልሁ ታላላቆችም ውኆች ተከለከሉ፥ ሊባኖስንም ስለ እርሱ አሳዘንሁት፥ የዱርም ዛፎች ሁሉ ስለ እርሱ ዛሉ።

Ver Capítulo



ሕዝቅኤል 31:15
8 Referencias Cruzadas  

እናንተ የጊልቦዓ ተራሮች ሆይ፤ በዚያ የኀያሉ ሰው ጋሻ ረክሶአልና፤ የሳኦል ጋሻ በዘይት መወልወሉ ቀርቶአልና፤ ጠልም ሆነ ዝናብ አይውረድባችሁ፤ የቁርባን እህል የሚያበቅሉም እርሻዎች አይኑራችሁ።


በዚያን ጊዜ የባሕር አለቆች ሁሉ ከዙፋኖቻቸው ይወርዳሉ፤ መጐናጸፊያቸውን ያስቀምጣሉ፥ ወርቀዘቦ ልብሳቸውንም ያወልቃሉ፤ መንቀጥቀጥን ይለብሳሉ፥ በመሬት ላይ ይቀመጣሉ፥ ሁልጊዜም ይንቀጠቀጣሉ፥ በአንቺም ይደነቃሉ።


አሁን በውድቀትሽ ቀን ደሴቶች ይንቀጠቀጣሉ፥ በባሕር ያሉ ደሴቶችም ከመጥፋትሽ የተነሣ ይደነግጣሉ።


በማጠፋህ ጊዜ ሰማዮችን እሸፍናለሁ፥ ከዋክብቶቻቸውንም አጨልማለሁ፤ ፀሐይን በደመና እሸፍናለሁ፥ ጨረቃም ብርሃንዋን አትሰጥም።


በዚያ ጊዜ የይሁዳና የኢየሩሳሌም ቁርባን እንደ ዱሮው ዘመንና እንደ ቀደሙት ዓመታት ጌታን ደስ የሚያሰኝ ይሆናል።